👉በቀጣይ 5 አመት ከ ኤክስፖርት የሚገኘው ገቢ በእጥፍ እንዲጨምር ነው የታቀደው።
ዛሬ በግብርና ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተጠራ መድረክ ይፋ የተደረገው ኢኒሼቲቭ የኢትዮጵያን የቡና ምርትና ምርታማነት ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እንዲሁም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ በከፍተኛ ደረጃ የሚያሻሽል አዲስ ሀገራዊ እቅድ መሆኑበተገልጿል።
በመድረኩ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ ምንም እንኳ የኢትዮጵያ የቡና ምርታማነት በሄክታር 8 ኩንታል ቢሆንም የዓለም አማካይ የቡና ምርታማነት በሄክታር 15 ኩንታል መሆኑን ጠቅሰዋል።
እንደ ብራዚልና ቪየትናም ያሉ ሀገራት ደግሞ በሄክታር ከ25 እስከ 27 ኩንታል ያመርታሉ።
ኢትዮጵያ የቡና መገኛና ለዓለም ያበረከተችው ውድ ስጦታ ብትሆንም፣ አሁን ላይ ያለው የምርት መጠን ከዓለም አቀፍ ደረጃ አንጻር ሲታይ አሁንም ዝቅተኛ ነው።
በመሆኑም በቀጣይ አምስት አመት ውስጥ በተቀመጠው ውጥን የምርት መጠኑን በሄክታር ወደ 21 ኩንታል ለማድረስ ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት።
ክቡር ሚኒስትሩ እንደጠቆሙት በሳይንስና ምርምር የታገዘ አዲስ አሰራር
አዲሱ የቡና ውጥን በርካታ መሰረታዊ ለውጦችን ያካተተ ሲሆን፣ ዋነኛው የምርምር ስራዎችን ማጠናከር ነው። ከዚህ በተጨማሪ
በሽታንና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም የሚችሉ፣ እንዲሁም ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ አዳዲስ የቡና ዝርያዎችን (ሀይብሪድ) ማውጣትና ማባዛት ላይ በትኩረት ይሰራል።
ለዚህም ስኬት በጅማ የግብርና ምርምር ማዕከል የቲሹ ካልቸር ማዕከል ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል።
በተመሳሳይ ከቡና ወጪ ንግድ 6 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት መታቀዱን ነው የቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) የተናገሩት።
ይህ ግብ በቀጣይ 5 አመት ለማሳካት የታቀደ ሲሆን የገቢ መጠኑን አሁን ካለበት 3 ቢሊየን ዶላር በእጥፍ የሚያሳድግ ነው።
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቆት አመታት የቡና ምርት እና ወጪ ንግድ ገቢ ላይ ከፍተኛ ሊባል የሚችል ግብ እያስመዘገበች ነው። ቡና አሁን ላይ ከወርቅ ቀጥሎ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ አስገኚ ነው።SECO

