ኢትዮጵያ ወደ ዱባይ የምትልከውን ጥሬ ወርቅ ልታቆም ነው

በኢትዮጵያ የሚመረተው ወርቅ በሙሉ ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እንደምትልክ የታወሳል፡፡ ሆኖም መንግስት የወርቅ ማንጠሪያ ማቋቋሙን ተከትሎ ወደ ዲባይ የሚልከውን ወርቅ እንደሚያቆም ነው የሚጠበቀው፡፡

የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ውሳኔን አስመልክቶ የብሄራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝ (ዶር) ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት የአገሪቱ የወርቅ ማንጠሪያ (refinery) በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ስራ ይገባል፡፡

ይህም ማለት የጥሬ ወርቅ ፋብሪካው ወደ ውጭ የሚላከውን ወርቅ ሙሉ ለሙሉ በአገር ውስጥ ማንጠር የሚያስችለው ነው የሚሆነው፡፡

በዚህም የተነሳ ለማንጠር ወደ ዱባይ የሚላከው ወርቅ በጠቅላላ በአገር ውስጥ መዘጋጀት የሚጀምር ይሆናል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ዋነኛ የኢትዮጵያ ወርቅ ገዥ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለቀለት ወርቅ ተረካቢ ወደ መሆን ትሸጋገራለች ነው የተባለው፡፡

ብሄራዊ ባንክ ቀደም ሲል በከፍተኛ ደረጃ እየገባለት የወርቅ ምርትን የጥራት ደረጃ ለማሳደግ እና ወርቅ ያልሆኑ ሌሎች ቁሶችን ለመለየት የሚያስችለው ዘመናዊ የምርመራ ስልት ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩ ይታወሳል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ የብሄራዊ ባንክ ለባህላዊ ወርቅ አቅራቢዎች ይሰጥ የነበረውን ከ5 እስከ 15 በመቶ ተጨማሪ የማበረታቻ ክፍያ ከቀጣዩ መስከረም ወዲህ ሙሉ ለሙሉ እንደሚያቆም ታውቋል፡፡

የአለምአቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባንኩ ነገረኝ ብሎ በ5ኛ ግምገማ ሰነዱ ይፋ እንዳደረገው ብሄራዊ ባንክ ባለፉት ጊዜያት የባህላዊ ወርቅ አቅራቢዎች ወደ ማእከላዊ ገበያ ወይም ብሄራዊ ባንክ የሚያቀርቡትን ወርቅ ከፍ እንዲያደርጉ እና ኮንትሮባንድ እንዲቀንስ በማሰብ በአለም ገበያ ላይ ተጨማሪ ፕሪሚየም እየሰጠ ነበር የሚገዛው፡፡

በአዲሱ እቅድ ይህ ተጨማሪ ከፍተኛ ክፍያ ይቋረጣል ነው የተባለው፡፡

የማክሮኢኮኖሚ ማሻሻያው በ2017 በጀት አመት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ እና የውጭ ምንዛሬ ገበያ በገበያ ይወሰን ከተባለ በኋላ ለመንግስት የሚገባው የወርቅ መጠን በከፍተኛ መጠን ጨምሮ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ምንጭ መሆን ችሏል::

በተጠናቀቀው በጀት አመት ብቻ ከወርቅ ወጪ ንግድ 5.5 ቢሊየን ዶላር ገቢ የተገኘ ሲሆን ይህም አገሪቱ ከሸቀጥ ኤክስፖርት በጠቅላላ ካገኘችው 11 ቢሊየን ዶላር የ ግማሽ ወይም 50 በመቶ ድርሻ የሚኖረው ነው፡፡  

በተመሳሳይ ብሄራዊ ባንክ በሂደት ከወርቅ ግብይት እየወጣ የንግድ ባንኮች እንዲቆጣጠሩት የታቀደ ሲሆን፡፡ ለዚህም ማእከላዊ ባንኩ እንዴት እና መቼ ከግብይት ይውጣ የሚለውን ስትራቴጂ እስከ ቀጣዩ ታህሳስ ወር ይፋ የሚደረግ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡SECO   

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories