የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) የመጀመሪያው ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ጥላሁን እስማኤል ካሳሁን ከኃላፊነት መልቀቃቸውን ተከትሎ ወ/ሮ ዮዲት ካሳ አዲሷ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተደርጋ ተሹማለች።
ጥላሁን ፤ ገበያውን ከምስረታው ጀምሮ ሙሉ አቅሙን ያሟላ የሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ እንዲሆን በማድረግ፤ በተቋም ግንባታ እና በገበያ ልማት ዘላቂ አሻራ ማሳረፋቸዉ ተገልጿል።

በኃላፊነት ዘመናቸው ታሪካዊ የሆነ የካፒታል ማሰባሰብ ሥራ በማጠናቀቅ፣ እንዲሁም የአስተዳደር፣ የሰው ሀይል እና የቴክኖሎጂ መሰረቶችን በመጣል ረገድ ወሳኝ ሚና በመጫወታቸውን የገበያው የዳይሬክተሮች ጨምሮ አስታውቋል።
አዲሷ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዮዲት ካሳ ገበያው ከፕሮጀክት ደረጃ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ የጉዞው አካል የነበሩ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም የቺፍ ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር እና የቺፍ ቢዝነስ ኦፊሰር ኃላፊነቶችን አገልግለዋል።
ወ/ሮ ዮዲት በአሁኑ ወቅት የተጀመሩ ቁልፍ ስራዎችን ወደፊት በማስቀጠል የሰድ ዓውጭ ኩባንያዎችን መሰረት በማስፋት፣ በገበያ ውስጥ ተሳትፎን በመጨመር እና የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ለኢኮኖሚያዊ ሽግግር ማፋጠኛ በማድረግ ላይ ያተኩራሉ ተብሎ ይጠበቃል።


