የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ካለው የማክሮ ኢኮኖሚ እና የፊስካል ተጋላጭነት አንጻር እንደ እውነተኛ የሀብት ፈንድ ሊያገለግል እንደማይችል አመለከተ። ባንኩ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት፣ እንደ እውነተኛ የሀብት ፈንድ ለመቆጠር ዘላቂ የበጀት ወይም የውጭ ንግድ ትርፍ ማግኘት የግድ መሆኑን ጠቁሟል።
ባንኩ፤ ኢትዮጵያ ባለችበት የዕዳ ጫና የህዝብ ገንዘብን ወደ ባህላዊ የቁጠባ ፈንድ ማዞር ለማህበራዊ አገልግሎቶች እና ለዕዳ ቅነሳ የሚደረገውን ወጪ አደጋ ላይ ይጥለዋል ብሏል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሀብት ትርፍን ከማስተዳደር ይልቅ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን አፈፃፀም ማሻሻል፣ የድርጅት አስተዳደርን ማጠናከር እና የግል ባለሀብቶችን መሳብ ላይ ማተኮር እንዳለበት ሪፖርቱ አሳስቧል።
ሆልዲንግሱ የተቋቋመው ከትርፍ ቁጠባ ሳይሆን ከልማት ድርጅቶች ንብረት እና ከግል ማደረግ ሂደቶች በመሆኑ፣ ከባህላዊ ፈንድ የተለየ መዋቅር እንዳለው ተገልጿል። የባንኩ ትንበያ እንደሚያሳይ ከሆነ ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ የፋይናንስ ማሰባሰብ ፈተናዎችን እየተጋፈጠች ትገኛለች
Breaking News
የአፍሪካ ልማት ባንክ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እውነተኛ የሀብት ፈንድ ሊሆን አይችልም አለ
Popular Categories


