በላይነህ ክንዴ ኢትዮጵያ ሆቴልን ሊያፈርሱት ነው

በኢትዮጵያ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ከተገነቡ ቀዳሚሆቴሎች አንዱ የሆነው ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ እንደሆነ ነው የተሰማው፡፡

ሆቴሉም እስከ መጪው ጥቅምት ወር ድረስ ሙሉ ለሙሉ  ፈርሶ ሌላ ግንባታ ይከናወንበታል ነው የተባለው፡፡

እ.ኤአ በ1963 የተገነባው ኢትዮጵያ ሆቴል በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዘመነ መንግስት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑን የአፍሪካ ህብረት ምስረታ ላይ ለመሳተፍ  ወደ አዲስ አበባ ለሚመጡ  መሪዎች ማረፍያ ሆኖ አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ መገንባቱ ነው ተጽፎ የሚገኘው፡፡

እንደ አዲስ ፎርቹን ዘገባ ሆቴሉን የገዛውና ሌላ ግንባታ ለማከናወን እንቅስቃሴ የጀመረው  በበላይነህ ክንዴ የሚመራው የቢኬ ግሩፕ ሲሆን ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴልን ማፍረስ ጀምሯል፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አአድ/OAU) ስብሰባዎችን በማስተናገድ ስራ የጀመረው  ባለ 5 ፎቅ ታሪካዊ ኢትዮጵያ ሆቴል ዋናው ህንፃ ሙሉ በሙሉ እንዲነሳ የተወሰነ ሲሆን፣ ከሆቴሉ ጋር የተያያዙ ሱቆች አስቀድመው እንዲለቁ ተደርጓል።

በ109 ክፍሎችና በ140 ሠራተኞች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ኢትዮጵያ ሆቴል በ2002 ዓ.ም በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በ94 ሚሊዮን ብር በቢኬ ግሩፕ በኩል የገዙት ሲሆን  በቦታው  ላይ ዘመናዊ ሕንጻ ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምረዋል፡፡seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories