ኢትዮጵያ በቴምር  ተገቢውን ምርት እያገኘች እንዳልሆነ ተነገረ

2ኛው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል በአፋር ክልል ሊካሄድ ነው።

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ

ኢትዮጵያ ለቴምር ልማት ተስማሚ የሆነ የአየር ጠባይ እና የመሬት ሀብት እንዳላትና በተለይም  በአፋር፣ በሶማሌ፣ በድሬዳዋ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በታችኛው ኦሞ ሸለቆ ያሉ ዝቅተኛ እና ቆላማ አካባቢዎች ለቴምር ዛፍ እድገትና ምርታማነት ተስማሚ እንደሆኑ በጥናት መረጋገጡ ነው የተነገረው።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር አሊ መሀመድ  ዛሬ በሰጡት መግለጫ 2ኛው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል ከመስከረም 10 እሰከ 12 በአፋር ክልል ይካሄዳል፡፡

ሀገሪቱ ከ5000 ሺህ እስከ 700 ሺህ  ሄክታር መሬት ማልማት የሚያስችል አቅም  ቢኖራትም   በአሁኑ ወቅት እየለማ ያለው 6 ሺህ ሄክታር ብቻ እንደሆነ ነው የተናገሩት።

ይህም ማልማት ከሚቻለው መሬት 1 ነጥብ 2 በመቶ ብቻ እንደሆነ ነው የገለጹት፡፡ በዚህ ምክንያት በቴምር  ተገቢውን ምርት እየተገኘ አይደለም ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ  የቴምር ምርትን በማስፋት ተገቢውን ምርት ለማግኘት የ10 አመት ስትራቴጂ ተነድፎ ወደ ስራ መገባቱን ነው የገለጹት፡፡

በኢትዮጵየያ ቴምር የሚያመርቱ አካባቢዎችን በጥናት የተለየ ሲሆን ዝርያ በማባዛት የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

ቀደም ሲል ቴምር ምርትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በዓመት 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ዶላር ይወጣ እንደነበር ያስታወሱት ፕሮፌሰር አሊ  አሁን ላይ  ቴምርን በሀገር ውስጥ ማምረት በመቻሉ  ወደ 650 ሺህ ዶላር ዝቅ ማለቱን አስረድተዋል።


በአለም አቀፍ ደረጃ የቴምር ምርት እና ንግድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚታይበት ዘርፍ ሲሆን እንደ ግብፅ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ኢራን፣ አልጄሪያ እና ኢራቅ ያሉ ሀገራት ከፍተኛውን የቴምር ምርት ለዓለም ገበያ የሚያቀርቡ ዋና ዋና አምራቾች ናቸው፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories