የዓለም ቁጥር አንዱ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መሪ ከሃላፊነት ለቀቁ

የኒቪዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ ስራ መልቀቅ አሜሪካና ቻይናን አፋጧል

የአለም ቁጥር አንዱ የረቀቁ ቺፕሶችን የሚያመርተው እና የዓለም የሰው ሰራሽ አስተውሎት Artificial intelligence AI ቁልፍ ዘዋሪ የሚሰኘው ኒቪዳ በመሪው ቅሌት ሲታመስ ሰንብቷል፡፡

የግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ ለቻይና ኩባንያዎች የቺፕስ አቅራቢ ከሆኑ ተቋማት ጋር ግንኙነት እንዳላት ከምትታመን አሊስ ሁዋንግ ጋር ከትዳራቸው ውጪ ማግጠዋል የሚል የምርመራ ዘገባ በኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ቀርቦባቸው ነበር፡፡

 ጋዜጣው ሴትየዋ የቻይና የደህንነት ሚስጥር አቀባይ ሰላይ ናት የሚል መረጃ ማከሉ የወሲብ ቅሌቱ ውስብስብ አድርጎት መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

ስመጥሩ ቢሊየነርና የኒቪዳ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ በትዳሬ ላይ ማግጫለሁ ብለው ለሰራተኞቻቻው በማሳወቅ በይፋ ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን የቅሌት ዝርዝሩ ቀጥሎ ሰውየው ከሚመሩት ተቋም አንድ የስራ ሃላፊ ጋር ተጨማሪ ግንኙነት እንዳላቸው ዳግም በኒውርክ ታይምስ መዘገቡ ጉዳዩን አወሳስቦታል፡፡

እናም ዋና ስራ አስፈፃሚው ከሚመሩት ኒቪዳ በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ መወሰናቸውን የኩባንያው ቦርድ አሳውቋል፡፡

የኒቪዳ የአክስዮን የድርሻ ገበያ እስከ 10 በመቶ መቀነሱ ሲዘገብ፣ ዋና ስራ አስፈፃሚው ለቻይና ትሰልላለች ከተባለች ሴት ጋር ግንኙነት አላቸው መባሉ ውዝግቡን ወደ ሃያላን ፍጥጫ አሸጋግሮታል፡፡

የቻይና መንግስት ዋና ስራ አስፈፃሚው የወሸሟት ሴት የቻይና ሰላይ ናት መባሉ መሰረተቢስ ውንጀላ መሆኑን በመግለፅ ይህ ስም ማጥፋት የቻይናን የቺፕስ ፍላጎትና ገበያ እንዲሁም ወትሮም ከአሜሪካ ጋር በውጥረት የተሞላው የቺፕስ ንግድን ቢጎዳ ያስተዛዝባል ብላለች፡፡

ከኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ ውጪ የሴትየዋ የቻይና ሰላይነት በአሜሪካ መንግስት እስካሁን በይፋ ያልተነገረ ሲሆን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ የኒቪዳ መሪ እጅግ መልካምና ጎበዝ ሰው ሲሉ ከጎናቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

የአለም ቁጥር አንድ ቢሊየነር ኤለን መስክ ኒቪዳ ትልቅ ሰው ነው ያጣው ጄንሰን ሁዋንግን የመሰለ የቴክኖሎጂ መሪ ማግኘት ፈታኝ ነው ሲል አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አመላክቷል፡፡

የዓለም ቴክኖሎጂ መሪ የሆነው የኒቪዳን ዋና ስራ አስፈፃሚ በሴት የማጥመዱ ጉዳይ የአለም ልዕለ ሃያልነት ፉክክር በቴክኖሎጂ እና በAI በተመሰረተበት በዚህ ወቅት ቻይናና አሜሪካ የቴክኖሎጂ ሚስጥሮች ላይ የሚያደርጉትን ሽኩቻ የሚያሳይ ተብሎለታል፡፡SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories