በዝናብ እጥረትና በነዳጅ ዋጋ መናር ሳቢያ በመጪው ዓመት 2.8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለምግብ እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለ

በኤልኒኖ የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በሚከሰት የዝናብ እጥረት እና በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መናር ሳቢያ፣ በመጪው የፈረንጆች ዓመት (2027) ተጨማሪ 2.8 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ለምግብ እጥረት ሊጋለጡ እንደሚችሉ ዓለም አቀፉ የምግብ ፖሊሲ ምርምር ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ።

አዲሱ የኢንስቲትዩቱ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ የአየር ንብረት መዛባቱ በግብርና ምርታማነት ላይ በሚፈጥረው መስተጓጎል ምክንያት 905 ሺህ ተጨማሪ ዜጎች ወደ ድህነት ሊገቡ ይችላሉ።

 የኢትዮጵያ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ዕድገትም ከተተነበየው ከ0.4 እስከ 1.1 በመቶ ሊቀንስ እንደሚችል ተገምቷል።

በዋናው የክረምት ወቅት በተለይም በሰሜንና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች በተከሰተው የዝናብ እጥረት፣ በደረቅ ደጋማ አካባቢዎች የግብርና ምርት በ9.6 በመቶ፣ በቆላማ አካባቢዎች ደግሞ በ6.5 በመቶ እንደሚቀንስ ጥናቱ አመላክቷል።

ይህ ሁኔታ የቤተሰቦችን የመግዛት አቅም በአማካይ በ1.9 በመቶ የሚያዳክም ሲሆን፣ ለምግብ እጥረት ከሚጋለጡት ዜጎች ውስጥ 76 በመቶው የገጠር ነዋሪዎች ይሆናሉ ተብሏል። ስለሆነም የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከሰኔ እስከ ነሐሴ 2019 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት፣ መንግስትና ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች ቀድመው አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተመራማሪዎቹ አሳስበዋል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories