ባንኮች ለአርብቶ አደሩ  ደፍረው ብድር ማቅረብ እንዳለባቸው ተገለጸ

የአርብቶ አደሩ ድምፅ እንዲሰማና ተገቢው የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠርለት እየሰራ እንደሚገኝ ፖስቶራሊስት ፎረም ኢትዮጵያ  አስታወቀ፡፡

ፎረሙ የአርብቶ አደሩ ጉዳይ ትኩረት እንዲያገኝ ከጋዜጠኞች ጋር የጋራ መድረክ አዘጋጅቶ የመከረ ሲሆን የፖስቶራሊስት ፎረም ኢትዮጵያ  ዋና ስራ አስፈጻሚ ተዘራ ጌታሁን ለኢቲ ቢዝነስ ቪው እንደገለጹት  በኢትዮጵያ ከጠቅላላው የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት ከ60 በመቶ በላይ የሚሸፍን በአርብቶ አደሮች የተያዘ ነው፡፡

ፎረሙ  አርብቶ አደሮች በዘላቂነት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ እንዲሁም በአካባቢያቸው  የመሰረተ ልማት እንዲስፋፋ ድምጽ በመሆን እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

መንግስት ለአርበቶ አደሮች ትኩረት በመስጠት ፖሊሲ አውጥቶ ወደ ተግባራ መገባቱን አስታውሰው ግንዛቤ ይዞ ፖሊሲውን መተግበር ላይ ክፍተት እንዳለ ገልጸዋል፡፡

ቀደም ሲል አርብቶ አደር አካባቢ በማህበራዊና ፖሊካዊ ጉዳዮች ትኩረት አላገኘም ነበር ያሉት ሀላፊው አሁን ላይ ለውጥ መምጣቱንና  በማዕከላዊው ፖለቲካ ተሳትፎአቸው እያደገና  ውሳኔ እስከ መስጠት  የደረሱ እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

የመገናኛ ብዙሀን አርብቶ አደሮች ተገቢው የኢኮኖሚ ትስስር እንዲፈጠርላቸው እንዲሁም አስፈላጊው መሰረተልማት እንዲዘረጋላቸው ድምጽ በመሆን መስራት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡

አርብቶ አደሮች  በአገሪቷ እንስሳት ሀብት አማካኝነት በኢኮኖሚ ላይ ያላቸው ሚና ከፍተኛ ቢሆንም ብዙም ተጠቃሚ ሲሆኑ አይታይም  የሚሉት የፖስቶራሊስት ፎረም ኢትዮጵያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ አብዲ አብዱላሂ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በእንስሳት ሀብት ወጪ ንግድ ላይ አርብቶ አደሮች መሰርት ቢሆኑም ከዘርፍ ተገቢውን ዋጋ እያገኙ አይደለም፡፡ በመሀል ያለው የገበያ ሂደት በደላሎች የሚመራና  ህጋዊነት የተከተለ ባለመሆኑ ለዘርፉ ተግዳሮት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል፡፡

አርብቶ አደሩን ማዕከል ያደረገ ፖሊሲ ቢያወጣም ንብረቱን አስይዞ መጠቀም እንዳልቻለ የሚናገሩት የቦርድ ሰብሳቢው ባንኮች ለአርብቶ አደሩ ብድር ለመስጠት መድፈር እንዳለባቸው አስታውቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከጠቅላላው የሀገሪቱ የቆዳ ስፋት ከ60 በመቶ በላይ የሚሸፍን በአርብቶ አደሮች የተያዘ ሲሆን አርብቶ አደሮች  በዋናነት በቆላማ  ክፍሎች እንደሚገኙና በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ (በተለይም ቦረና፣ ጉጂ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ እና ከረዩ አካባቢዎች) እንዲሁም በደቡብ ኢትዮጵያ (ደቡብ ኦሞ) በስፋት ይኖራሉ፡፡

በሌሎች አካባቢዎች. በጋምቤላ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎችም በቁጥር አነስተኛ የሆኑ አርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር ማህበረሰቦች እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories