ላይፍታይም ፕሮፐርቲ ትሬዲንግ በቦሌ ግራንዲየር  ያስገነባቸው ቤቶች ለደንበኞች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አስረከበ

 ድርጅቱ  በሚክስድ ማርሻል አርት ስፖርት ታዋቂ የሆነውን ቢኒያም ሽብሬን  ለዓለምአቀፍ እንዲሁም   ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ለሃገር ውስጥ  ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰይሟል።

የላይፍታይም ፕሮፐርቲ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር የድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ደግሰው አያና እንደገለጹት ላይፍታይም ፕሮፐርቲስ ትሬዲንግ ምስረታው በሀገር ውስጥና  በውጭ ሀገር በብዙ ልፋትና ትጋት ሀብት ያፈሩ ዜጎች ገንዘባቸውን ያለምንም ስጋትና መንገላታት ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

ከ4 ኪሎ ወዳጅነት ፓርክ ፕሮጀክት ጀምሮ እስከ  የቦሌ ግራንዲየር የካርታ ርክክብና የአዲሱ «ቦሌ አይከኒክ» ሳይት ማስጀመሪያ ድረስ የድርጅቱ ጉዞ ታማኝነትን ያረጋገጠ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በዛሬው ዕለት ድርጅቱ የቦሌ ግራንዲየር ያስገነባው ባለ 22 ወለል ህንጻ የይዞታ ማረጋገጫ  ካርታ ለደንበኞቹ አስረክቧል

የ«ቦሌ አይከኒክ (Bole Iconic)» ፕሮጀክት   3B+G+16 ሲሆን የተቋሙ የጥራትና የታማኝነት ጉዞ ቀጣይ ምዕራፍ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

 ድርጅቱ  ከዚህ ቀደም ከገነባቸው የመኖሪያ ህንጻዎች በግንባታ ሂደት ያገኘውን ልምድ ተጠቅሞና አዳዲስ እሴት ጨምሮ በላቀ ሁኔታ የሚገነባው ዘመናዊ የመኖሪያ ህንጻ እንደሆነ አስረድተው አመቺ በሆነ ስፍራ እና በዘመናዊ መልክ የሚገነባ ሀንጻ ግንባታና ሽያጭ  መጀመሩን አስታውቀዋል።

ድርጅቱ  ብራንዱን ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሃገር ደንበኞቻችን ጋር የሚያገናኙ ድልድዮች እንዲኖሩት በማሰብ የብራንድ እምባሳደሮችን በጥንቃቄ  በመምረጥ  የማሀበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪ  ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) ለሃገር ውስጥ

እንዲሁም አለምአቀፍና ዳያስፖራ ግንኙነት መጠናከር እንደድልድይ ሆኖ እንዲያገለግል በሚክስድ ማርሻል አርት ስፖርት በዓለም አቀፍ መድረክ ታዋቂ የሆነውን ቢኒያም ሽብሬን የላይፍታይም ፕሮፐርቲስ ዓለምአቀፍ ብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሰይሟል።SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories