ኢትዮጵያ በሀገር ውስጥ ታሪፍ ለኤርትራ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ እንደሆነባት ነው የተገለጸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በዛሬው የምክር ቤት ውሎአቸው ካነሱት ነጥቦች መካከል የኤርትራ ጉዳይ አንዱ ነው፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ለኤርትራ መንግስት የመንገድ ግንባታ ለመስራት እንዲሁም የኤሌክትሪክ ሀይል መሰመር በመዘርጋት በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ታሪፍ ክፍያ እንዲፈም ለቀረበለት ጥያቄ የእንቢታ መልስ እንደሰጠ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡
በኤርትራ መንግስት መዝገበ ቃላት ውስጥ ውስጥ ልማት የሚል ቃል የለም ሲሉ ከሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት ከኤርትራ መንግስት ሁለት ነገሮችን እንደሚፈልግ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንደኛው የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያን ጠላቶች ማስታጠቅ ማቆም እንዲሁም ሁለተኛው ለጋራ ልማት አብሮ መነሳት ነው ይህ ካልሆነ የኤርትራ መንግስት በማይታረም ስህተት ውስጥ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡SECO


