ድርጅቱ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በዲጂታል መሠረተ ልማት እና በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታሪኩ ደምሴ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለማስፋፋት እንዲሁም የዲጂታል ልማት ለማፋጠን ቁርጠኛ እንደሆነች ገልጸዋል፡፡
ኩባንያው የአረንጓዴ ቴሌኮም ኢኒሼቲቮች፣ ውጤታማ የኃይል አጠቃቀምን እና ዘላቂ መሠረተ ልማትን በማስፋፋት አካባቢ ጥበቃን ያማከለ ዲጂታል ዕድገትን ለማረጋገጥ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው የጃፓን የውጭ ንግድ ድርጅትን (JETRO) ጨምሮ ግንባር ቀደም የጃፓን ተቋማትና ኩባንያዎችን ከሚወክለው ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር፤ በዲጂታል መሠረተ ልማት፣ በአረንጓዴ ቴክኖሎጂ፣ በኢነርጂ መፍትሔዎች እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ዘርፎች ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ውይይት አካሄደዋል።
የጃፓኑ ልዑክ በኢትዮ ቴሌኮም በመሠረተ ልማት፣ በኃይል፣ በኢንጂነሪንግና በኢንዱስትሪ ዘርፎች የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ ስትራቴጂያዊ አጋርነት ለመፍጠር ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል።

የልዑክ ቡድኑ የኢንተለጀንት ኦፕሬሽንስ ማዕከላችንን (IOC) እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መሙያ ጣቢያዎችን በመጎብኘት የኔትወርክ ኦፕሬሽንና የቁጥጥር አሰራሩን ተመልክቷል፡፡
በውይይቱ ላይ ጄትሮ፣ አይቲኦቹ ኮርፖሬሽን፣ ሳንዮ፣ ሶጂትዝ፣ ሚትሱይ ኦ.ኤስ.ኬ. ላይንስ፣ ዮኮጋዋ ኤሌክትሪክ፣ ኒፖን ኮይ፣ ካናዴቪያ፣ ያዛኪ ኢነርጂ ሲስተም እና ሂዮኪ እ ኔሌሎች ዓለም አቀፍ የጃፓን ኩባንያዎች ተሳትፈዋል።SECO


