ዳሸን ባንክ ለ15ኛ ጊዜ የ“ዘ ባንከር” ሽልማትን አሸነፈ

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ፈር ቀዳጅ የሆነውን የዳሸን ሱፐር አፕ መተግበሪያ በማስተዋወቅ የዲጂታል ባንክ አገልግሎትን አንድ እርምጃ ያራመደው ዳሸን ባንክ ለ15ኛ ጊዜ የ“ዘ ባንከር” ሽልማትን ማግኘት ችሏል፡፡

ከተለያዩ አገራት የተወጣጡ ባንኮችን በተለያዩ የአፈጻጸም መለኪያዎች በመመዘን ዓለም አቀፍ ዕውቅና የሚሰጠውና በእንግሊዙ ፋይናንሻል ታይምስ የሚታተመው ዘ ባንከር መጽሔት፣ ዳሸን ባንክ ሁሉን በአንድ የሆነ መተግበሪያ በማስተዋወቁና ለአገሪቱ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ያመጣውን አበርክቶ እንደ ቁልፍ መስፈርት በመውሰድ ለ15ተኛ ጊዜ የ2025 የኢትዮጵያ የዓመቱ ምርጥ ባንክ በሚል ሰይሞታል፡፡

ሽልማቱን በእንግሊዝ ለንደን ከተማ ተገኝተው የተቀበሉት የዳሸን ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው ዓለሙ እንደገለጹት “ዳሸን ባንክ የአመቱ የኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ ተብሎ መሸለሙ ባንኩ የኢንዱስትሪውን ቀጣይ ጉዞ በፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ለመቅረጽ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋግጣል።” ብለዋል፡፡

ባንኩ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፈር ቀዳጅ  በመሆን የሀገሪቱን የመጀመሪያ የባንክ ሱፐር አፕ እና የዙሪያ የቢዝነስ አውቶሜሽን ማሽንን አስተዋውቀናል።” ያሉት አቶ አስፋው፣ “ወደፊትም፣ ሁሉን አካታች፣ ቀልጣፋ እና በዲጂታል መንገድ የተገነባ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ለመፍጠር እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories