ካምቴል እና ኢትዮ ቴሌኮም በካሜሩን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችል ውል አሰሩ

የካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (ካምቴል) የካሜሩንን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የኮንትራት ስምምነት በካሜሮን -ያውንዴ ተፈራርመዋል፡፡

ሁለቱ ኦፕሬተሮች የተፈራረሙት ስምምነት ኢትዮ ቴሌኮም የካሜሩንን የለውጥ ጉዞ ለማገዝ እና የካምቴል ግቦችን ዕውን እንዲሆኑ ለማገዝ ከፍተኛ የአማካሪነት አገልግሎት፣ የልምድ ልውውጥ  ተሞክሮዎችን በማቅረብ እና ያለውን ልምድ በማካፈል ጭምር በዘርፉ አብሮ የመስራት ዕድልን ይፈጥራል ተብሏል።

የአጋርነት ስምምነቱ በዋናነት የሞባይል ገንዘብ ኢኖቬሽን የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማሳደግ  በ”ብሉ መኒ” የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አገልግሎት በጋራ መስራት፣ብሄራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት (የህዝብ አገልግሎቶችን ዲጂታል ማድረግና ብሄራዊ የመንግሥት ክላውድ እንዲቋቋም መደገፍ፣የኔትወርክ መዘመን ለላቀ የግንኙነት ጥራት  የ4G፣ 5G ኔትወርክን እና አዳዲስ መፍትሄዎችን ለማቅረብ የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ድጋፍ መስጠት፣ተቋማዊ ለውጥ በዋናነት የመረጃ ሥርዓቶችን በማዘመን፣ አሰራርን አውቶሜሽን በማድረግ፣ ደንበኛ-ተኮር ባህልን በማጎልበት ረገድ ድጋፍ በማድረግ የካምቴልን ተቋማዊ ሽግግር መደገፍየሚያካትት እንደሆነ ቅዳሜ ገበያ ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ  የትብብር አድማሱን በማስፋት በኢንተርፕራይዝ መፍትሔዎች፣ በዲጂታል የአኗኗር ዘይቤ አገልግሎቶች፣ በኢንተርኮኔክት ማዕቀፎች እና ተጨማሪ ዕሴት ያላቸው አገልግሎቶች እና ስትራቴጂያዊ ትብብር መፍጠርን የሚያካትት እንደሚሆን ተጠቁሟል።

በስምምነቱ አማካኝነት ካምቴል (CAMTEL) የካሜሩንን ዲጂታላይዜሽን በማፋጠን አካታች ኢኮኖሚ የመገንባት አቅሙን የሚያጎለብት ሲሆን፤ ይህም በኢትዮ ቴሌኮም ‘ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ’ መሰረት ከአፍሪካዊ ኦፕሬተሮች ጋር በአጋርነት የዲጂታል አፍሪካን ጉዞ ለማፋጠን እና ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተገልጿል፡፡©SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories