ኩባንያው እንዳስታወቀው ሰኔ 30 ቀን 2025 በተጠናቀቀው የፋይናንስ ዓመት ሕይወት ነክ፣ ሕይወት ነክ ካልሆነው እና ከጀነራል ታካፉል የኢንሹራንስ ዘርፎች የሰበሰበው አጠቃላይ አረቦን ብር ከ2.753 ቢሊየን ብር በላይ ነው።
ከተሰበሰበው አጠቃላይ የአረቦን መጠን ውስጥ አብዛኛው ወይንም 2.57 ቢሊዮን ብር ሕይወት ነክ ካልሆነው የኢንሹራንስ ዘርፍ፣ 141 ሚሊዮን ብር ከሕይወት ኢንሹራንስ ቀሪው ብር 31.9 ሚሊዮን ብሩ ደግሞ ከታካፉል ኢንሹራንስ የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በተጠናቀቀው በጀት አመት ከግብር በፊት 1 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን ነው ያስታወቀው።
ኩባንያው ከግብር በኋላ ያገኘው የተጣራ ትርፍ ደግሞ 843 ሚሊዮን ብር ሲሆን ይህም ከቀዳሚው አመት ጋር ሲነፃፀር የ79 በመቶ ብልጫ አስመዝግቧል።
የኩባንያው የተከፈለ ካፒታል 1.34 ቢሊዮን ብር፣ ጠቅላላ ሃብቱ ደግሞ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡©SECO


