ባንኩ ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ከ85.5 ቢሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከነበረዉ የ26 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡
አጠቃላይ የባንኩ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ብር 56.4 ቢሊዮን በ25% በማደግ 70.3 ቢሊዮን ብር እንደደረሰ ተነግሯል፡፡
የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በ6% በማደግ 6.88 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ አጠቃላይ ካፒታል ደግሞ 11.6 ቢሊዮን ብር መድረሱን ባንኩ አስታውቋል፡
ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ 12.36 ቢሊዮን ብር ጠቅላላ ገቢ ያገኘ ሲሆን፣ ይህም ከእቅድ የ105% ብልጫ ሲኖረው ጠቅላላ ወጪው 9.79 ቢሊዮን ብር እንደነበር አስታውቋል።
አፈጻጸሙም ከታክስ በፊት 2.6 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ እንዳስገኘ ባንኩ ገልጿል፡፡
የባንኩ የተቀማጭ ሂሳብ 6.9 ሚሊዮን ድርሷል ሲደርስ የዲጂታል አገልግሎቶች ተጠቃሚ ደንበኞቻችን ቁጥር 5.7 ሚሊዮን መድረሱ ተጠቁሟል።
ሚልኪ የደመወዝ ዱቤ ክፍያ እና ሚልኪ፣ አሁን ይግዙ፤ በኃላ ይክፈሉ ባሉ አማራጭ አገልግሎቶች አማካኝነት አርሶ-አደሮችን፣ ሴቶችን እና ወጣቶችን ትኩረት ያደረጉ ሚልኪ የዲጂታል ፋይናንሲንግ ፕላትፎርሞችን በመታገዝ የሚሰራ፣ ያለዋስትና ብድር የሚሰጥበት መተግበሪያ ሥራ ላይ ማዋሉን አስታውቋል።
የሚልኪ አገልግሎት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ከ80 ሺህ በላይ ተበዳሪዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ሲሆን፣ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱን አስታውቋል፡፡©SECO


