ገዳ ባንክ በቅርቡ ባካሄደው 4ተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤው ላይ ባሳወቀው መሠረት፣ በ2017 በጀት ዓመት ከግብር በፊት 448 ሚሊዮን ብር ትርፍ በማግኘት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ208.3 በመቶ አስደናቂ ዕድገት አስመዝግቧል።
የባንኩ የተጣራ ትርፍም 342.8 ሚሊየን ብር ደርሷል። አጠቃላይ ሀብቱ ወደ 10.1 ቢሊዮን ብር ያደገ ሲሆን፣ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘቡ ደግሞ 7.8 ቢሊዮን ብር ደርሶ በ92.5 በመቶ ብልጫ አሳይቷል።
ባንኩ ለደንበኞች ከወለድ ነፃ ብድርን ጨምሮ 1.8 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን አስታውቋል። በዲጂታል ባንኪንግ ዘርፍም የኦምኒ ቻናል አገልግሎትን ወደ ስራ ማስገባቱን በመግለጽ፣ ጠቅላላ የዲጂታል ተጠቃሚ ደንበኞቹን ከ114,000 በላይ አድርሶ 4.3 ቢሊየን ብር መገላበጡን ገልጿል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 15 አዳዲስ ቅርንጫፎች በመክፈት ጠቅላላ ቅርንጫፎቹን 100 ያደረሰው ገዳ ባንክ፣ የደንበኞቹ ብዛት 575,977 መድረሱን ተናግሯል።Seco


