ሚስጥራዊው የዝናብ ስርዓት በምስራቅ አፍሪካ ለዘመናት ለዘለቀው ድርቅና እርጥበት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ

ተመራማሪዎች ባለፈው ምዕተ ዓመት በአፍሪካ ቀንድ ውስጥ ለአስርት ዓመታት የሚቆዩ ደረቅ እና እርጥብ ወቅቶች መንስኤ ሊሆን የሚችል ሚስጥራዊ የዝናብ ስርዓት ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።

ይህ ግኝት በዓለም ዙሪያ የዝናብ ምንጭ በሰብል ምርት ላይ ያለውን ወሳኝ ተፅዕኖ የሚያመላክት ሲሆን በተለይም ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን ለመጠበቅ አዲስ መንገድ ሊከፍት ይችላል።

በኔቸር ሰስተይነቢሊቲ መጽሔት ላይ በወጣው ሪፖርት፣ ዝናብ ከውቅያኖሶች ይልቅ ከየብስ (ከአፈር፣ ከሐይቆች እና ከደን) በሚመጣበት ጊዜ ሰብሎች ከድርቅ የመከላከል አቅማቸው እንደሚቀንስ አረጋግጧል።

በግኝቱ መሰረት፤ ከየብስ የሚመነጨው ዝናብ ብዙውን ጊዜ ደካማ እና ብዙም አስተማማኝ ስላልሆነ፣ በሰብሎች ወሳኝ የሕይወት ዑደት ጊዜያት ላይ ከፍተኛ የሆነ የድርቅ ውጥረት እንዲፈጠር ያደርጋል።

ጥናቱ ለ20 ዓመታት ያህል በሳተላይት መረጃ ላይ በመመሥረት፣ ከዝናቡ ከአንድ ሦስተኛ (1/3) በላይ ከየብስ የመጣ ከሆነ ሰብሎች ለድርቅ ከፍተኛ ስጋት እንደሚጋለጡና የአፈር እርጥበት እና ምርት እንደሚቀንስ አሳይቷል።

በተለይም ምስራቅ አፍሪካ በድርቅ የተመታ የግጦሽ መሬትና ሰብል እያጋጠማት ነው። የሰብል መሬት መስፋፋት እና የደን መጨፍጨፍ የተፈጥሮ የእርጥበት ክምችቶችን በማሟጠጥ፣ የየብስ ዝናብን የማይታመንነት ይጨምራሉ።

ተመራማሪዎቹ የመሬት አጠቃቀም ልምዶች ካልተሻሻሉ በስተቀር ይህ አዝማሚያ ለረጅም ጊዜ የምግብ ዋስትና ማሽቆልቆልን ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ተመራማሪዎቹ ደኖችን መጠበቅ እና መሬትን በተሻለ መንገድ ማስተዳደር የዝናብ መረጋጋትን ለማገዝ እና የሰብል ምርትን ለመጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል።Seco

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories