በኢቢቪ ዘጋቢ
ተጨማሪ የቴሌኮም ኩባንያ በመሆን ወደ ኢትዮጵያ የገባው ሳፋሪኮም ከመነሻውም በአገሪቱ የሚሰራበት ታሪፍ እንደማያዋጣው ሲገልፅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።
ሆኖም ፍሬህይወት ታምሩ የሚመሩት ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት አመታት ከፍተኛ የታሪፍ ቅናሽ በማድረግ ለደንበኞቹ ተመጣጣኝ የድምፅ እና ዴታ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።
ትላንት ታህሳስ 15 ቀን ሳፋሪ ኮም ይፋ እንዳደረገው በስራ እና ኢንቨስትመንት ወጪ መናር በዴታ አገልግሎቱ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።
ምንጮች እንደሚገልፁት ኩባንያው ኢትዮ ቴሌኮም ጭማሪ እንዲያደርግ በይፋ ጥይቋል።
ይሁን እንጂ በተለይ ከምንዛሪ ለውጥ ጋር ተያይዞ በተለይ በዴታ አገልግሎት ላይ ወጪ መጨመሩን ባለሞያዎች ቢናገሩም የኢትዮ ቴሌኮም ውሳኔ አለመታወቁን ገልፀዋል።
ትላንት የሳፋሪኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒተር ንድጌዋን አስከትለው ወደ አዲስ አበባ የመጡት የኬንያው ፕሬዝደንት ዊልያም ሩቶ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች ዙርያ መወያየታቸውን ገልፀው ነበር።
በውይይታቸው በሁለቱ መንግስታት ድጋፍ ኩባንያዎቹ ስልታዊ ጥምረት ፈጥረው በቀጠናው በኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ ስምምነት መደረሱን ነው የገለፁት።
በውይይታቸው የኢትዮ ቴሌኮም የበላይ የሆነው ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታየ እንዲሁም የዘርፉ ተቆጣጣሪ የሆነው ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የበላይ ባልቻ ሬባ ተገኝተው ነበር።©SECO

