ለዋጋው ማሽቆልቆል የምርት መጨመር እንደምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ከሳምንት በፊት የወጣው የUSDA ሪፖርት እንደሚያመለክተው የ2025/26 የዓለም የቡና ምርት ከላፈው ዓመት ምርት የ3.5 ሚሊዮን ኬሻ ብልጫ በማድረግ 178.8 ሚሊዩን ኬሻ ደርሷል፡፡ በተመሳሳይ ሪፖርት እንደተቀመጠው የፍጆታ መጠንም በተመሳሳይ ዓመት 173.9 ሚሊዮን ኬሻ እንደደረሰ ያሳል፡፡
ለዓለም የቡና ዋጋ ማሽቆልቆል ከሚጠቀሱ ዋነኛ ምክንያቶች ውስጥ በቡና አብቃይነታቸው ቀዳሚ የሆኑት ብራዚል፣ቬትናም፣ኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ምርት መጨመር፣ እንዲሁም የአሜሪካ ታሪፍ መነሳት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡
ለብራዚል ግብርና ሚኒስቴር ተጠሪነቱ የሆነው CONAB እንዳስታወቀው የብራዚል የ2026/27 ምርት ግምት ይፋ ያደረገ ሲሆን ከ71 እስከ 74.4 ሚሊየን ኬሻ ምርት ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በቬትናም Vicofa የተባለው የቡናና የካካዎ ማህበር ባስቀመጠው ግምት ካለፈው ዓመት አንፃር የ10% የምርት መጠን ይጨምራል፡፡
እንዲሁም የኢትዮጵያ በ500,000 ኬሻ፤ የኢንዶኔዥያ ደግሞ 1.7 ሚሊዮን ኬሻ ምርት ጭማሪ ያሳያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራም በብራዚል ላይ የታሉት የ40% ታሪፍ መነሳቱ የቡና ዋጋ በዓለም አቀፋ ገበያ እንዲወርድ ሌላው ተጨማሪ ምክንያት እንደሚሆን ነው የተነገረው፡፡
የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ደንብ ጥብቅ መስፈርቶች EUDR መተግበሪያ ጊዜ በአንድ ዓመት መራዘሙ የዓለም የቡና ዋጋ ለመቀነሱ ተጨማሪ ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል፡፡
አምስቱ በቡና ምርት ቀዳሚ የሆኑት ሀገራት ማለት ብራዚል፣ ቬትናም፣ ኮሎምቢያ፤ ኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ብቻቸውን የዓለምን የቡና ምርት 73% ይሸፍናሉ፡፡@seco


