የኢትዮጵያ ፖስታ ያበለጸጋቸውን “ሳጥን አልባ (Virtual)” የመልዕክት አገልግሎት እና “የፖስታ ገበያ” የኢ-ኮሜርስ መተግበሪያዎችን ነው ወደ ስራ ያስገባው፡፡
መተግበሪያዎቹ ተቋሙ እየሰራበት የነበረውን ልምድ ከዘመኑ የፈጠራ ስራዎች ጋር በማዋሃድ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ መፍትሄዎችን ለደንበኞች ማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡፡
አዲሱ የቨርቹዋል ፖስታ ሳጥን አገልግሎት የደንበኞችን የሞባይል ስልክ ቁጥር እንደ ዲጂታል አድራሻ እንዲያገለግል የሚያደርግ ሲሆን ከየትኛውም የዓለም ክፍል የሚላኩ መልዕክቶች እና ጥቅሎች በስልክ በሚደርሳቸው ፈጣን ማሳወቂያ መከታተል የሚያስችልና ባሉበት ቦታ ሆነው በቤት ለቤት አገልግሎት እንዲረከቡ እንደሚያስችል ተገልጿ፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ፖስታ ድርጅት አባል የሆነችው 1900 ዓ.ም. ሲሆን ሥራው የተጀመረው በ1886 ዓ.ም. ግድም እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። ዳግማዊ አጤ ምኒልክ በ1885 ዓ ም የካቲት 10 ቀን ከፖስታ ማኅበር ለመግባት ደብዳቤ ቢጽፉ “መጀመሪያ የፖስታ ሥራ ማካሄ ዱን ይጀምሩ” የሚል መልስ ያገኙ ሲሆን ምኒልክም በፈረንሣይ አገር ፓሪስ ከተማ ውስጥ በመልካቸው የተቀረፀ ቴምብር በ1886 ዓ.ም. በጥቅምት ወር አሳትመው ገበያ ላይ በማዋል ሥራውን ማስጀመር ችለዋል፡፡@seco


