ንግድ ባንኮች ለብድር ከያዙት ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ 1 በመቶ የሚኾነውን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንድ ለመግዛት እንዲያውሉት የሚያስገድደውን መመሪያ  ከታህሳስ 22/2018 ጀምሮ መነሳቱን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች ለብድር ከያዙት ገንዘብ ውስጥ ቢያንስ 1 በመቶ የሚኾነውን ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ቦንድ ለመግዛት እንዲያውሉት የሚያስገድደውን መመሪያ አንስቷል።

 ባንኩ ባወጣው መግለጫ በተሻሻለው መመሪያ መሠረት አስገዳጁ የባንኮች የቦንድ ግዥ ከታህሳስ 22/2018 ጀምሮ መነሳቱን አስታውቋል።

እንደ ዋዜማ ዘገባ መመሪያው ከመሻሻሉ በፊት ከልማት ባንክ ቦንድ የገዙ ባንኮች ግን ለአስተዳደራዊ ምቹነት ሲባል በተሻረው መመሪያ መሠረት እንደሚቀጥሉ ባንኩ ገልጧል።

 ብሄራዊ ባንክ፣ ንግድ ባንኮች መንግሥታዊው የፖሊሲ ባንክ ከኾነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በግዳጅ ቦንድ እንዲገዙ የሚያስገድደውን መመሪያ ከአራት ዓመት በፊት ያወጣው፣ ለረጅም ጊዜ ትላልቅ የልማት ፕሮጀክቶች በቂ ካፒታል ለማሰባሰብና ባንኮችም በዚህ ረገድ አስተዋጽዖ እንዲያደርጉ ለማስቻል ነበር።

ኾኖም የግዳጅ የቦንድ ግዥው ባንኮች ትርፍ የሚያስገኙ ብድሮችን በማበደር አቅማቸው ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል የሚል ትችት ሲቀርብበት ቆይቷል::@SECO

Related

በግሎባል ባንክ የ18 ሚሊዮን ብር የአክሲዮን ግዢ እና የአመራር ውዝግብ አዳዲስ ጥያቄዎችን አስነሳ

በቅርቡ ከፍተኛ የአመራርና የመልካም አስተዳደር ውዝግብ ውስጥ የገባው ግሎባል...

ዘመን ባንክ የኢንተርፕራይዞች የአሰራር ክፍተት ለመሙላት እየሰራ ነው

የአነስተኛና መለስተኛ ኢንተርፕራይዞች አቅም ማጎልበት ትኩረት እንደሚሻ ተጠቁሟል የዘመን ባንክ...

አንበሳ ባንከ በተፈጠረበት ጫና ብሄራዊ ባንክ ጣልቃ እንዲገባ ጠየቀ

አዲሱ ቦርድ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለም ተብሏል ባለፈው አመት የተደረገውን...

ዘምዘም ባንክ የሀብት መጠኑ ከ29 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን አስታወቀ

ባንኩ 1.56 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡ ተጠቁሟል። በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ዘምዘም ባንክ...

የዳሽን ባንከ አብዛኛው እንቅስቃሴ ወደ ወረቀት አልባ መግባቱን ባንኩ አስታወቀ

የሱፐር አፕ እለታዊ የገንዘብ ዝውውር 3.7 ቢሊየን ብር ተሻግሯል በአብዱልሰመድ...

Popular Categories