47.6 በመቶ ያህሉ የኢትዮጵያ ስደተኞች የመንግሥት ድጋፍ ተቀባይ ናቸው” – ፕሬዝዳንት ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አሜሪካ ውስጥ የሚኖሩ 47.6 በመቶ ያህሉ የኢትዮጵያ ስደተኞችና ቤተሰቦቻቸው የአሜሪካ መንግሥት ድጋፍ (Welfare) ተቀባይ መሆናቸውን ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም 71.9 በመቶዎቹ ትውልደ ሶማሊያውያን በተመሳሳይ በመንግሥት ድጋፍ ውስጥ የታቀፉ መሆናቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተዘግቧል።

​ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን መረጃ ያጋሩት፣ በተለይ በሶማሊያውያን ስደተኞች ላይ ያነጣጠረ ወቀሳ ሲያቀርቡ ከቆዩ በኋላ ነው። ሶማሊያውያንና ትውልደ ሶማሊያውያን በብዛት በሚኖሩባት በሚኒሶታ ግዛት ውስጥ፣ የሕፃናት እንክብካቤን ጨምሮ መንግሥት የሚያቀርበው ነፃ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚመዘበር ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ ሲወነጅሉ መቆየታቸውን ዋዜማ ዘግቧል።

​ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ግዛቲቱ ውስጥ የመንግሥትን ነፃ ድጋፍ በተጭበረበረ መንገድ የሚጠቀሙ ትውልደ ሶማሊያውያን ዜጎችን ከሀገር እንደሚያባርሩ ጭምር በመዛት ላይ ይገኛሉ። ይህ የፕሬዝዳንቱ መግለጫ በአሜሪካ በሚኖሩ የስደተኛ ማህበረሰቦች ዘንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኗል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories