ፍላተርዌቭ የናይጄሪያውን የፊንቴክ ስታርትአፕ ‘ሞኖ’ን በ40 ሚሊዮን ዶላር ጠቀለለ

የአፍሪካ የክፍያ ቴክኖሎጂ ግዙፍ የሆነው ፍላተርዌቭ (Flutterwave)፣ የናይጄሪያውን የፋይናንስ መሠረተ ልማት አቅራቢ “ሞኖ” (Mono) ከ25 እስከ 40 ሚሊዮን ዶላር በሚገመት ዋጋ መግዛቱን አስታወቀ። ይህ ግዢ በአፍሪካ የፊንቴክ ዘርፍ የታየ ትልቅ ውህደት ተደርጎ ተወስዷል።

ሞኖ በናይጄሪያ የ”ኦፕን ባንኪንግ” መሠረተ ልማትን በማስተዋወቅ ፈር ቀዳጅ ሲሆን፣ ደንበኞች የፋይናንስ መረጃዎችን እንዲያጋሩ፣ ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ እና ከአንድ የባንክ ሂሳብ ወደ ሌላ በቀጥታ ክፍያ እንዲፈፅሙ የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ በሮችን (APIs) ያቀርባል።

የፍላተርዌቭ መስራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኦሉግቤንጋ አግቡላ እንደገለጹት፣ ክፍያ፣ መረጃ እና መተማመን ተነጣጥለው ሊታዩ አይችሉም። ግዢው ኩባንያው በአፍሪካ ይበልጥ የተገናኘ እና የተቀናጀ የፋይናንስ ሥርዓት ለመገንባት ለያዘው ግብ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርለት ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ፍላተርዌቭ ኩባንያውን ቢገዛውም፣ ሞኖ አሁን ባለው አመራር እና የሥራ ቡድን ራሱን ችሎ ሥራውን እንደሚቀጥል ተገልጿል። የግዢው ሂደት በአክሲዮን ልውውጥ የተከናወነ ሲሆን፣ አንዳንድ የሞኖ ቀደምት ባለሀብቶች ካወጡት መነሻ ካፒታል እስከ 20 እጥፍ የሚደርስ ትርፍ ማግኘታቸው ተነግሯል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories