በአሜሪካ በ1.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት እጅግ ግዙፍ የሊቲየም ክምችት ተገኘ

በአሜሪካ ኦሪገን እና ኔቫዳ ግዛቶች ድንበር ላይ በሚገኝና ከ16 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በፈነዳ “ሱፐርቮልካኖ” (Supervolcano) ስር፣ በዓለም ላይ በግዝፈቱ ቀዳሚ ሊሆን የሚችል የሊቲየም ማዕድን ክምችት መገኘቱን ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

“ማክደርሚት ካልዴራ” ተብሎ በሚጠራው በዚህ ጥንታዊ የእሳተ ገሞራ ተፋሰስ ውስጥ የተገኘው ማዕድን፣ ከ20 እስከ 40 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን የሚመዝን ሊቲየም ሊይዝ እንደሚችል ተገምቷል።

ይህም በገንዘብ ሲሰላ እስከ 1.5 ትሪሊዮን ዶላር የሚያወጣ ሲሆን፣ አሜሪካ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ባትሪና ለቴክኖሎጂ ምርቶች የሚያስፈልጋትን የሊቲየም አቅርቦት በአገር ውስጥ ለመተካት ትልቅ ዕድል የሚፈጥርላት ነው።

ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ በፈሳሽ መልክ የነበረው ሊቲየም በእሳተ ገሞራው አመድና በጭቃማ ድንጋዮች (Claystone) ውስጥ ተከማችቶ ለሚሊዮን ዓመታት ቆይቷል።

 “ሃይቴክ ሚነራልስ” የተባለው ኩባንያ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው የአሰሳና የቁፋሮ ሥራዎችን የጀመረ ቢሆንም፣ የማዕድን ቁፋሮው በአካባቢው ሥነ-ምህዳር፣ በውኃ አቅርቦትና በሀገር በቀል ማህበረሰቦች ቅዱስ ስፍራዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ እያጋጠመው ይገኛል።

ሊቲየም ለታዳሽ ኃይልና ለዘመናዊ መከላከያ መሣሪያዎች ቁልፍ ግብዓት በመሆኑ፣ ግኝቱ በዓለም አቀፍ የኃይልና የጂኦፖለቲካ መድረክ ላይ የአሜሪካን ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያሳድግ እንደሚችል ተነግሯል። ሆኖም ማዕድኑን ከጭቃማ ድንጋይ ውስጥ ለይቶ ለማውጣት የሚጠይቀው የቴክኖሎጂ ውስብስብነትና የአካባቢ ጥበቃ ሥጋቶች ለፕሮጀክቱ ትልቅ ፈተና እንደሚሆኑ ተመልክቷል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories