የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት በበጀት ዓመቱ ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ካቀዳቸው ከተሞች መካከል ስምንቱ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓትን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረጋቸውን ገለጸ።
ቅዳሜ ገበያ ከኢንስቲትዩቱ የደረሳት መረጃ እንደሚያመለክተው ፤ አዳማ፣ ሐረር፣ ጂማ፣ ደብረ ብርሃን፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ኮምቦልቻ እና ቢሾፍቱ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ተደርገዋል። በአሁኑ ወቅት የእነዚህ ከተሞች የሲስተም ልማት ሥራ ተጠናቆ በመስክ ላይ የሙከራ ትግበራ እየተከናወነ ይገኛል።
ይህ ዘመናዊ አድራሻ ሥርዓት በቅርቡ በይፋ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር የተገለጸ ሲሆን፤ የከተሞቹ ነዋሪዎችም ሆኑ እንግዶች ሥርዓቱን በመጠቀም የሚፈልጉትን ቦታ በቀላሉ ማግኘት እንደሚችሉ ተመላክቷል።
SSGI ከዚህ የዲጂታል አድራሻ ሥርዓት ጋር ተያያዥነት ያለውንና የተሻሻለውን የሞባይል አፕሊኬሽን በቅርቡ ለተጠቃሚዎች እንደሚለቅ አስታውቋል።@SECO


