ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ የኒውክሌር ኃይል ማመንጨት እንደምትጀምር አስታወቀች

የኢትዮጵያ ኒውክሌር ኢነርጂ ኮሚሽን የአገሪቱን የኃይል ዋስትና ለማረጋገጥና ዘላቂ ልማትን ለመደገፍ በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በኒውክሌር ቴክኖሎጂ የታገዘ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ለመጀመር ማቀዱን ይፋ አድርጓል።

የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር አብዱልረዛቅ ዑመር እንደገለጹት፣ ምንም እንኳን በዓለም አቀፍ ተሞክሮ የኒውክሌር ኃይል ልማት እስከ 15 ዓመታት የሚፈጅ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ እንደ ቻይና ያሉ አገራትን ተሞክሮ በመውሰድ ሂደቱን በማፋጠን በአሥር ዓመት ውስጥ ግቡን ለማሳካት በትኩረት እየሰራች ትገኛለች።

ለዚህ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ስኬታማነት ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሙን በኃላፊነት የሚመራ ብሔራዊ ተቋም አስቀድማ ማቋቋሟንና አስፈላጊው የዝግጅት ሥራ መጀመሩን ምክትል ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።

ሂደቱ መሠረተ ልማት ከመገንባት ባለፈ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የኒውክሌር ደኅንነትና የጥበቃ መስፈርቶችን ማሟላት ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሲሆን፣ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን ለሰላማዊ ዓላማ መጠቀም ለጤና፣ ለኢንዱስትሪ እና ለግብርና ዘርፎች ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories