ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን መግዛቱን አስታወቀ
ዋቢ ሸበሌ ሆቴል አፄ ኃይለስላሴ ልጃቸው ልዑል መኮንን በመኪና አደጋ ምክንያት በድንገት ማረፋቸውን ተከትሎ ለልጅ ልጆቻቸው መተዳደሪያ እንዲሆን የሰሩላቸው መሆኑ ይነገራል።

ዋቢ ሸበሌ ሆቴል በ1957 ዓም ተጀምሮ በ1960 ዓም ተጠናቆ ስራ ቢጀምርም በወታደራዊው መንግስት በ1967 ዓ.ም ተወርሶ በመንግስት ስር ሆኖ አገልግሎት እየሰጠ ቆይቷል፡፡
ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ በሚሊኒየሙ መባቻ ለቀድሞ ባለቤቶቹ ማለትም ለልዑል መኮንን ልጆች መመለሱ አይዘነጋም።
ኢትዮጵያ 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ ለተሳታፊዎች ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ ይሆናል ተብሏል።

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።
የሆቴሉ አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ አቶ ጀማል ተናግረዋል።@SECO


