ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ይኖር የነበረ “ፓራንትሮፐስ” የተባለ የቅድመ ሠው ዝርያ ተገኘ 

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከ2.6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት ይኖር የነበረ “ፓራንትሮፐስ” የተባለ የቅድመ ሠው ዝርያ  በአፋር ክልል ሚሊ-ሎጊያ በተባለ የፓሊዮአንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ማግኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ግኝቱ ኢትዮጵያ ለቅድመ ሰው ቅሪት ፍለጋና ለሰው ዘር አመጣጥ ያላትን ጠቀሜታ አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን የበለጠ ያረጋገጠ ግኝት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአሜሪካ የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ በሆኑት ፕሮፌሰር ዘረሰናይ አለምሰገድ የተመራ የጥናት ቡድን ጥናቱን ይፋ ሲያደርግ እንዳስታወቀው ከ 2.6 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የኖረና ከዚህ ቀደም በአፋር ተገኝቶ የማያውቅ የቅድመ ሠው ዝርያ ማግኘት ችለዋል፡፡

ፓራንትርፐስ የሚል ሥያሜ ያለው ይህ አዲሱ ግኝት ሚሌ ሎጊያ የፓሊዮአንትሮፖሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ መገኘቱን የተገኘ ሲሆን ግኝቱም በታዋቂው ኔቸር የሳይንስ መፅሄት ላይ ይፋ ሆኗል፡፡

ግኝቱ፣ ፓራንትሮፐስ እንደ አውስትራሎቲከስ እና ሆሞ ሁለገብ እና ሠፊ ቦታ (ከደቡብ አፍሪካ እስከ አፋር) ያካለለ ዝርያ እንደነበር ከማሣየቱ በተጨማሪ  አፋር በርካታ የቅድመ ሠው ዝርያዎች የነበሩበት፣ ግንባር ቀደም የፓሊአንትሮፖሎጂ መካነ-ቅርሥ ስፍራ የመሆኑን አስተሳሰብ የሚያጠናክር፤  ኢትዮጵያ ለቅድመ ሠው ቅሪት ፍለጋና ለሠው-ዘር አመጣጥ ጥናት ያላትን ልዩ ጠቀሜታ አጉልቶ የሚያሣይ  ኢትዮጵያም የሠው ዘር መገኛ መሆኗን የበለጠ ያረጋገጠ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

“ምድረ ቀደምት” ተብላ የምትጠራው ኢትዮጵያ ለሠው ዘር አመጣጥ ጥናት ልዩ አስተዋፅኦ ማበርከቷን  በመላ አገሪቱ ያሉ በርካታ መካኑ-ቅርሶች አስከ 6 ሚሊዮን ዓመታት የሚደርሱ ተከታታይነት ያላቸው አያሌ የቅድመ ሠው ዘር (hominins) ቅሪተ አካላትና የድንጋይ መሣሪያዎች መገኛ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህ ረገድ፤ የአፋር መካነ ቅርሶች ልዩ ቦታ እንደሚይዙም ተናግረዋል፡፡

የተገኘው ግኝት ለየት የሚያደርገው ትልልቅ  መንጋጋዎች ጥርሶችና የሚመገበው ምግብ ሳይቀር የተለየ መሆኑን የገለፁት ፕሮፊሰር ዘረሰናይ እስካሁን ኢትዮጵያዊ ስያሜ እንዳልተሰጠውና ሙሉው ጭንቅላት ሲገኝ ስያሚው እንደሚሰጠው አብራተዋል፡፡

በአሜሪካ የቺካጎ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሉሲ ልጅ እየተባለች የምትጠራውን የሰላም ቅሬተ አካል ያገኙ ተመራማሪ መሆናቸው የሚታወስ ነው።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories