የዳንጎቴ ነዳጅ ማጣሪያ የሚጠበቀውን ያህል ተጽዕኖ ማሳደር አልቻለም ተባለ

በላቁ ሀገራት ውስጥ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች በቋሚነት መዘጋታቸው የዓለምን የነዳጅ አቅርቦት መዋቅርና የገበያ ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ እየቀየረው መሆኑን ‘ክፕለር’  የተሰኘው የንግድ መረጃ ተንታኝ ድርጅት በቅርቡ ባወጣው ጥናት ገልጿል።

ተቋሙ እንደገለጸው፣ ከስዊዝ ቦይ በስተ ምዕራብ የሚገኙና በቀን 900,000 በርሜል ነዳጅ የማጣራት አቅም ያላቸው ፋብሪካዎች በቋሚነት ከሥራ መውጣታቸው፣ ቀደም ሲል በዘርፉ ያጋጥሙ የነበሩ ድንገተኛ የአቅርቦት እጥረቶችን ለመቋቋም የሚረዳውን የተጠራቀመ ኃይል እንዲሸረሸር አድርጎታል።

ይህ የማጣራት አቅም ማጣት ከፍተኛ ተጽዕኖ ያስከተለ ሲሆን፣ ጥቂት ማጣሪያዎች ብቻ በሥራ ላይ መቆየታቸው በማንኛውም ጊዜ የሚከሰት የሥራ መቋረጥ በነዳጅ ዋጋና አቅርቦት ላይ ትልቅ ቀውስ እንዲፈጥር ምክንያት ሆኗል።

በተለይም የአትላንቲክ ተፋሰስ ሀገራት በ2026 መጀመሪያ ላይ ትልቅ መዋቅራዊ ለውጥ ውስጥ መግባታቸውን የጠቀሰው ክፕለር፣ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ ወደ 800,000 በርሜል የሚጠጋ የማጣራት አቅም በቋሚነት መዘጋቱን አመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት የዓለም የነዳጅ ገበያን ለማረጋጋት በሁለት ግዙፍ አዳዲስ ማጣሪያዎች ማለትም በናይጄሪያው የ650,000 በርሜል አቅም ባለው ዳንጎቴ እና በሜክሲኮው የ340,000 በርሜል ዶስ ቦካስ ማጣሪያዎች ላይ ከፍተኛ ተስፋ ተጥሏል። ይሁን እንጂ የናይጄሪያው ዳንጎቴ ማጣሪያ ምንም እንኳ የሀገር ውስጥ ገበያን ለማርካት ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ በዓለም ገበያ ላይ ይጠበቅ የነበረውን ያህል ለውጥ ማምጣት እንዳልቻለ ተገልጿል።

ለዳንጎቴ ማጣሪያ አፈጻጸም መገደብ ዋነኛው ምክንያት በማጣሪያው ዋና የልወጣ ሥርዓት ላይ ያጋጠመውና እስካሁን ያልተፈታ የሜካኒክ ብልሽት መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ ቴክኒካዊ ችግር የማጣሪያውን የማምረት አቅም ከ60 እስከ 65 በመቶ ብቻ እንዲወሰን በማድረጉ፣ በምዕራባውያን ሀገራት የታየውን የማጣሪያ ፋብሪካዎች መዘጋት ተከትሎ የተፈጠረውን ክፍተት በሚፈለገው ደረጃ ለመሙላት እንዳላስቻለው ሪፖርቱ አብራርቷል።

በዚህም ምክንያት የዓለም የነዳጅ ምርቶች አቅርቦት እንደጠበበና የንግድ ትርፉም ባለፈው አንድ ዓመት እንደነበረው ከፍ ብሎ እንዲቀጥል አድርጎታል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories