አሜሪካ እና ህንድ ታሪካዊ የንግድ ስምምነት ተፈራረሙ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረውን የንግድ ውጥረት የሚፈታና አዲስ የኢኮኖሚ ትብብር የሚፈጥር ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።

በዚህ ስምምነት መሰረት፣ አሜሪካ በህንድ ምርቶች ላይ ጥላው የነበረውን የ50 በመቶ ታሪፍ ወደ 18 በመቶ ዝቅ ያደረገች ሲሆን፣ ይህም ህንድ ከሩሲያ ዘይት በመግዛቷ ምክንያት ተጥሎባት የነበረውን የ25 በመቶ ቅጣት የሚያነሳ ነው።

በምላሹም ህንድ ከሩሲያ ነዳጅ መግዛቷን በማቆም በአሜሪካ እና በቬንዙዌላ ምርቶች ለመተካት ከመስማማቷም በላይ፣ ከ500 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸውን የአሜሪካ የኢነርጂ፣ የቴክኖሎጂ እና የግብርና ምርቶች ለመግዛት ቃል ገብታለች።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህ ስምምነት ለሁለቱ ሀገራት ታላቅ ድል መሆኑን ገልጸው፣ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ለማቆም በሚደረገው ጥረት ላይም አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በበኩላቸው፣ ስምምነቱ ለ1.4 ቢሊዮን የህንድ ህዝብ ትልቅ እድል የሚፈጥርና “በህንድ የተሰሩ” ምርቶች ወደ አሜሪካ ገበያ በቀላሉ እንዲገቡ የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ ደስታቸውን ገልጸዋል።

 ይህ በአሜሪካ እና በህንድ መካከል የተደረገው ስምምነት ህንድ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የነፃ ንግድ ስምምነት ባደረገች በሳምንት ጊዜ ውስጥ የተፈጸመ ሲሆን፣ በዓለም አቀፍ የንግድ ገበያና በአሜሪካ አክሲዮን ገበያ ላይ መነቃቃትን ፈጥሯል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories