የአፍሪካ ሀገራት የውጭ ዕዳ ክፍያ በ2026 ከ90 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሊያልፍ እንደሚችል ተገለጠ

የአፍሪካ መንግሥታት በፈረንጆቹ 2026 የሚጠበቅባቸው የውጭ ምንዛሬ ዕዳ ክፍያ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ፣ በሀገራቱ የውጭ ምንዛሬ ክምችትና በኢኮኖሚ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ ጫና ሊፈጥር እንደሚችል ኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ሬቲንግስ አስጠነቀቀ።

​ተቋሙ ባወጣው የአፍሪካ ሉዓላዊ ሀገራት ትንበያ፣ የመንግሥታት የውጭ ዕዳ ክፍያ እ.ኤ.አ ከ2012 ጋር ሲነጻጸር በሦስት እጥፍ ማደጉን አመልክቷል። እንደ ሪፖርቱ ግምት ከሆነ፣ ዘንድሮ የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ ከ90 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ዕዳ ክፍያ ይጠበቅባቸዋል።

ከዚህ ግዙፍ የዕዳ ክፍያ ውስጥ ሲሶውን (27 ቢሊዮን ዶላር ገደማ) የምትሸፍነው ግብፅ ስትሆን፣ አንጎላ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ናይጄሪያም ከፍተኛ ክፍያ የሚጠበቅባቸው ሀገራት ተርታ ተሰልፈዋል።

ምንም እንኳን በአህጉሪቱ የሚታየው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፍላጎትና የብድር ደረጃ መሻሻል ተስፋ ሰጪ ቢሆንም፣ የዕዳው መጠን ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት አንጻር በአማካይ በ61 በመቶ ከፍ ብሎ እንደሚቀጥልና ይህም ሀገራቱ አማራጭ የፋይናንስ ምንጮችን እንዲፈልጉ ጫና እንደሚፈጥርባቸው ተመልክቷል።SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories