የባህረ ሰላጤው አገራት እና ቱርክ በምስራቅ አፍሪካ ያላቸው ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው

የባህረ ሰላጤው አገራትና ቱርክ በምስራቅ አፍሪካ ያላቸውን የኢኮኖሚና የደህንነት ተጽዕኖ በከፍተኛ ሁኔታ እያሰፉ እንደሚገኙ ተገለፀ ።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቱርክ፣ ኳታር እና ኩዌት በአጠቃላይ በምስራቅ አፍሪካ የ75 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስትመንት ያደረጉ ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በ47.4 ቢሊዮን ዶላር አንደኛውን ደረጃ ይዛለች።

ኤምሬትስ በተለይ በሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ እና ኢትዮጵያ ውስጥ በኢነርጂ፣ በመሠረተ ልማት እና በእርሻ ዘርፎች ላይ ሰፊ ተሳትፎ እያደረገች ሲሆን፣ በበርካታ አገራት ውስጥም የወደብ አስተዳደር ውሎችን በመያዝ በቀይ ባሕርና በሕንድ ውቅያኖስ ላይ ያላትን ተጽዕኖ እያጠናከረች ትገኛለች።

በሌላ በኩል ሳዑዲ አረቢያ ስትራቴጂካዊ ትኩረቷን በጅቡቲ ላይ በማድረግ 13 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በነዳጅ ማጣሪያና በሎጂስቲክስ ማዕከላት ላይ መድባለች። ቱርክ ደግሞ በመሠረተ ልማት በተለይም በባቡር መስመር ግንባታ እና በደህንነት ዘርፍ የላቀ ሚና እያገኘች መጥታለች።

ቱርክ በኢትዮጵያ፣ በታንዛኒያ እና በኡጋንዳ ግዙፍ የባቡር ፕሮጀክቶችን በማከናወን ላይ ስትሆን፣ ለቀጠናው አገራት የሰው አልባ ተዋጊ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) በማቅረብም ቀዳሚ ሆናለች።

 በተለይ በሶማሊያ ያለው የቱርክ ወታደራዊ ካምፕ እና የጸጥታ ትብብር በአገሪቱ ውስጥ ያላትን የፖለቲካ ተሰሚነት ከፍ አድርጎታል።

ይሁን እንጂ ይህ እየጨመረ የመጣው የውጭ ተዋናዮች ተሳትፎ በቀጠናው ላይ አሉታዊ ጥላ እያሳረፈ መሆኑን የአፍሪካ ስትራቴጂካዊ ጥናት ማዕከል ሪፖርት ይጠቁማል። የአገራቱ የጥቅም ግጭትና ፉክክር በተለይ በሱዳን እየታየ እንዳለው የርስ በርስ ጦርነትን በማባባስ እና ለተፋላሚ ወገኖች መሣሪያ በማቅረብ ረገድ የሚጫወቱት ሚና ለአካባቢው መረጋጋት ስጋት ሆኗል።

ምንም እንኳን ኢንቨስትመንቶቹ ለምስራቅ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ዕድል ይዘው ቢመጡም፣ የአገራቱ ከፍተኛ የዕዳ ጫና እና በውጭ ኃይሎች ላይ የሚኖራቸው ጥገኝነት ለወደፊት የፖለቲካ ነፃነታቸው ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል ተመላክቷል።@SECO

Related

በኤሌክትሪክ የምትንቀሳቀስ የዓለማችን ግዙፏ የዕቃ ጫኝ መርከብ

ንብረትነቷ የቻይና የሆነችውና 10 ሺህ ቶን ጭነት የመሸከም አቅም...

ሰሊጥ 21 ሺህ ብር በመሸጥ ከፍተኛ ዋጋ አስመዘገበ

ዋጋው ከቀደመው አመት 20 በመቶ ጭማሪ ሊያሳይ ችሏል ባለፉት ጥቂት...

የዓለም እድገት ወደ 2.6 በመቶ ዝቅ እንደሚል ተተነበየ

በጄኔቫ ይፋ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የንግድና ልማት ድርጅት (አንክታድ)...

በኒውዚላንድ በታክስ ማጭበርበር የተከሰሰችው አዛውንት በኢትዮጵያ ደካማ ኢንተርኔት ማሳበቧ ተገለፀ

ከኒውዚላንድ እየመጡ የሚገኙ ዘገባዎች እንዳመላከቱት  ከሆነ ሄለን ፉአታሃ የተባለች...

የኢራን ጦርነት የኢኮኖሚ ውድቀትን እያባባሰ ነው

ነዳጅ እና ውሀ ማጣሪያዎች እየተደበደቡ ነው። የኢራን እና እስራኤል፣ አሜሪካ...

Popular Categories