የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የአፍሪካ ሀገራት የራሳቸውን አህጉራዊ የፋይናንስ ድጋፍ ሥርዓት ሊዘረጉ እንደሚገባ አሳሰበ።
በሳዑዲ አረቢያ እየተካሄደ በሚገኘው “የአሉላ አዳጊ ኢኮኖሚዎች ጉባኤ” ላይ የተሳተፉት የባንኩ ገዢ እዮብ ተካልኝ ፤ የአፍሪካ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ካለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ የደህንነት መረብ ተጠቃሚ የመሆናቸው ዕድል እጅግ ውስን መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም ምክንያት ብዙዎቹ ሀገራት በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ክምችት እና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ድጋፍ ላይ ብቻ እንዲወሰኑ መገደዳቸውን ጠቁመዋል።
ይህንን ችግር ለመቅረፍ የአፍሪካን ነባራዊ ሁኔታና ተጋላጭነት ያገናዘበ፣ በተመሳሳይ ጊዜም ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ሥርዓት ጋር የተሳሰረ የቀጠናዊ ፋይናንስ ስምምነት መመስረት ለኢኮኖሚ ጥንካሬ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።@SECO


