ቅዳሜ ገበያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘችው መረጃ እንደሚያሳየው በሶማሌ ክልል ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ የተገነቡ አራት የፀሃይ ኃይል ፕሮጀክቶች ተመረቀው 24 ሰዓት አገልግሎት መሥጠት ጀምረዋል፡፡
በዲግ፣ በኑስደሪቅ፣ በጋሻሞ እና በምርቃን የተገነቡት እነዚህ የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች፤ የጤና እና የትምህርት ተቋማትን ጨምሮ ከ9 ሺ 500 በላይ ደንበኞችን የ24 ሰዓት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው፡፡
አራቱ ፕሮጀክቶች በድምሩ 1 ነጥብ 8 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፤ ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ 20 ነጥብ 42 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 78 ነጥብ 46 ኪ.ሜ ዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም 21 የተለያዩ አቅም ያላቸው ትራንስፎርመሮች ተተክለዋል፡፡

ከ940 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ወጥቶባቸው የተገነቡት እነዚህ ፕሮጀክቶች፤ ሙሉ ወጪው የተሸፈነው ከአለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ብድር ነው፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ 38 የጸሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ የሚገኝ ሲሆን ከዚህም ውስጥ በሶማሌ ክልል 8 የፀሀይ ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡@SECO


