በ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ላደርግ ነው አለ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

በዓለምሰገድ እስጢፋኖስ

በአፋር ክልል በአፍዴራና ዳሎል አካባቢ ላሉ የጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 21 አዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮችን 24 ሰዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ግንባታ ፕሮጀክት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡ 

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ በኢትዮጵያ ገንዘብ ከ2.4 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን፤ ከዚህ ውስጥ 16 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በአፍሪካ ልማት ባንክ እንዲሁም 84 ሚሊየን 627 ሺህ 401 ብር ደግሞ በአገልግሎቱ በኩል የሚሸፈን እንደሆነ ተገልጿል፡፡ 

ፕሮጀክቱ 375 ኪ.ሜ የመካከለኛ የኤሌክትሪክ መስመርና 93 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የ85 ትራንስፎርመሮች ተከላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

እስካሁን በተከናወነው ስራ 278 ነጥብ 34 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመርና 33 ነጥብ 5 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ እንዲሁም የ29 ትራንስፎርመሮች ተከላ ተጠናቋል፡፡ በዚህም 8 መንደሮችንና አንድ ፋብሪካ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ አገልግሎቱ አስታቋል፡፡

የፕሮጀክቱ አጠቃላይ አፈፃፀም 84 ነጥብ 46 መድረሲ ያስታወቀው ተቋሙ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ስራ በተያዘው በጀት ዓመት በማጠናቀቅ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጥ እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ በቀጣይም በአካባቢው በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የግል ድርጅቶችን በማበረታታትና የማህበረሰቡን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በማነቃቃት በቀጣይ ለሚከናወነው ሰፊ የኤሌክትሪክ ማዳረስ ስራ መሰረት የሚጥል እንደሆነ ቅዳሜ ገበያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

Popular Categories