ጠረጴዛ ላይ የተበተነው የሰራተኞች የበአል ቦነስ

ቻይናዊው ኩባንያ በአመታዊ የሰራተኞች ግብዣ ላይ ለሰራተኞች የቻላችሁትን ያህል ዘግናችሁ ውሰዱ ብሎ በጠረጴዛ ላይ የበተነው  በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ቦነስ/ጉርሻ አሰጣጥ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ስቧል፡፡

ቻይና በዜጎቿ ትልቅ ግምት በሚሰጠው እና ለሳምንታት በሚቆየው የአዲስ አመት ክብረ በአል ላይ ትገኛለች፡፡

ለበአል ለዛውም ለአዲስ አመት ቦነስ መስጠት በኩባንያዎች በአገራችንም አልፎ አልፎ የተለመደ ነው፡፡

በተለይ ትርፋቸው ሰማይ ለደረሱ ኩባንያዎች ጠቀም ያለ ጉርሻ መስጠት አዲስ ላይሆን ይችላል፡፡

ካተረፉት ላይ ከፍተኛውን ድርሻ ለሰራተኛ በቦነስ መልክ ማከፋፈል ግን የሚታሰብ አይደለም፡፡

የእቃ ማንጓጓዣ ክሬን የሚያመርተው የቻይና ኩባንያ ግን ይሄን አድርጎታል::

ኩባንያው ከአመታዊ ትርፉ 70 በመቶውን ወይም ወደ 26 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ነው ለሰራተኞቹ ‘ይመቻችሁ!’ ብሎ የሰጠው፡፡

ይሄን ዜና የሰሙ ብዙዎች ኩባንያው እጅግ ቸር መሆኑን ሲገልፁ ቢሰማም…

እንዳይመስላችሁ ገንዘብ መስጠት ማን ይወዳል ያለው የኩባንያው ባለቤት ቹይ ፔይጁን ይልቁኑ የሰራተኞቼን የብር እጥረት መረዳቴ ነው እንዲህ እንድናረግ ያስገደደኝ ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ኩባንያው ቦነሱን የሰጠበት (ለነገሩ የረጨበት! መንገድ ማለት ይሻላል) ደግሞ እጅግ አስገራሚ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው

በቻይና ሄናን ግዛት ቻንግዩዋን ከተማ አርብ  ቀን የካቲት 6፣ 2018 ዓም ሄናን ኩዋንግሻን ክሬን የተሰኘው ኩባንያ አመታዊ የሰራተኛ የራት ግብዣ አዘጋጅቷል፡፡

ድል ካለው የአዲስ አመት እራት በተጨማሪ ለ7 ሺ ሰራተኞቹ 60 ሚሊየን ዩዋን (8.7 ሚሊየን ዶላር) በጉርሻ መልክ እንዲከፋፈል ማድረጉ ደግሞ የግብዣውን ድባብ እና ደስታ እጥፍ ድርብ እንዲሆን አድርጎታል፡፡  

ይልቁንም የግብዣው እለት የተቀረጸ እና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨ እጅግ አነጋጋሪ የሆነ ቪዲዮ ግን ይበልጥ ጉዳዩ ትክረት እንዲስብ አድርጎታል፡፡

በቪዲዮው ሰራተኞች በረጅም ጠረጴዛ ላይ የተበተነ ብር ሲቆጥሩ ሌሎች ደግሞ የታሰረ ገንዘብ እንደምንም ይዘው ለመሄድ ወደዛ ወደዚ ሲሉ ያሳያል፡፡

ምንድነው ነገሩ ያሰኛል

የኩባንያው ባለቤት ለሰራተኞቹ ቀደም ሲል በግብዣው እየተጠሩ ከተሰጣቸው ገንዘብ በተጨማሪ ጠረጴዛ ላይ የተበተነውን ገንዘብ መሸከም እስከቻሉ እንዲወስዱ ማድረጉ ነው አጃይብ ያሰኘው፡፡

በዚህም በጠቅላላው ከአመታዊ ትርፉ ማለትም ከ40 ሚሊየን ዶላር ግድም 70 በመቶ የሚሆነውን ወይም 26 ሚሊየን ዶላሩን ሰራተኞች ለኑሮ መደጎሚያቸው እንዲከፋፈሉ ነው ኩባንያው ያደረገው፡፡

ይህ የቸርነት ተግባር ለነገሩ ለኩባንያው ሆነ ለባለቤቱ አዲስ አለመሆኑ የተዘገበው፡፡

እኤአ በ2024 ከአመታዊ 38 ሚሊየን ዶላር ትርፉ ድርጅቱ ለሰራተኞቹ 25 ሚሊየን ዶላር (66 በመቶ) ግድሙን በጉርሻ አከፋፍሏል፡፡

በተመሳሳይ አምና ማርች ኤይት (8) ሲከበር ለ2ሺ ሴት ሰራተኞቹ እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሳችሁ ሲል 230 ሺ ዶላር የሚሆን ዩዋን ጉርሻ እንዲከፋፈሉ አደርጓል፡፡   

የኩባንያው ባለቤት ቹይ ፔይጁን 99 በመቶ ድርሻ የያዙበት የክሬን አምራች እና አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ እኤአ በ2002 ተመስርቶ በ130 አገራት ይንቀሳቀሳል፡፡

‘መስጠት አብልጦ የሚወደው አለቃ’ የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ባለቤት፣ “የቤት እና መኪና እዳ ያናጠረባቸውን ወጣት ሰራተኞች ሸክም ማቃለል እንጂ ገንዘብ የመስጠት ፍቅር አይደለም፣” የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡

እንዲያም ሆኖ አንዳንዶች በዚች ምድር የተፈጠረ አምላክ መሆኑን ሲገልጹ፡፡ “ትክክለኛ የድርጅት ማስታወቂያ ይሏል እንዲህ ነው!“ ሲሉ ጉዳዩን የሰሙ ሌሎች የባለቤቱን ብልህነት እና የሰራተኛ አያያዝ እውቀት አድናቆት ቸረውታል፡፡

ቸርነቱ የበዛ ነው ያሉም አልጠፉም፡፡

ከዚህ ድርጅት ማን ይለቃል!

ማንስ ይሰርቃል!

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories