ሞዛምቢክ ብሔራዊ አየር መንገዷን ለመታደግ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ድጋፍ ጠየቀች

የሞዛምቢክ መንግሥት ለዓመታት ከፍተኛ ኪሳራና የአሠራር ችግር ሲፈታተነው የቆየውን ብሔራዊ አየር መንገዷን (LAM) መልሶ ለማቋቋም እና ለማነቃቃት የኢትዮጵያ አየር መንገድን ሙያዊ ድጋፍና ልምድ ለመጋራት ፍላጎት እንዳላት ገለጸች።

የሀገሪቱን መገናኛ ብዙሃን ጠቅሶ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ ሞዛምቢክ ይህንን የአጋርነት ጥያቄ ያቀረበችው አየር መንገዷ ካለበት ከፍተኛ የዕዳ ጫና ወጥቶ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ነው።

 ጥያቄው በዋናነት የአሠራር ተሞክሮን መቅሰም፣ ስልታዊ ዕቅዶችን መንደፍ እና የሰው ኃይል ልማትን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል።

የሞዛምቢክ አየር መንገድ አብራሪዎቹን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የልህቀት ማዕከል  ለማሠልጠን ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው ተጠቁሟል።

ይህም የአየር መንገዱን የቴክኒክ ብቃት ከፍ ለማድረግና የደህንነት መስፈርቶችን ለማሟላት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል።

በኢትዮጵያ የሞዛምቢክ አምባሳደር ኑኖ ቶማስ ስለ ጉዳዩ ሲያስረዱ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ ባለቤት ናት፤ እኛ ደግሞ የራሳችንን አየር መንገድ የማነቃቃት ትልቅ ህልም አለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካለምንም ተነስተው ዛሬ ካሉበት የልህቀት ደረጃ ላይ በመድረሳቸው፣ ከእነሱ በላይ የምንማርበት የተሻለ ቦታ የለም” ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ቀዳሚውና በዓለም አቀፍ ደረጃም ተወዳዳሪ የሆነ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።

 አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ለተለያዩ የአፍሪካ አገራት ብሔራዊ አየር መንገዶች (እንደ ማላዊ፣ ቶጎ እና ዛምቢያ ያሉ) መሰል የቴክኒክ እና የማኔጅመንት ድጋፎችን በማድረግ እንዲሁም በአጋርነት በመሥራት ይታወቃል።

ሞዛምቢክ ይህንኑ የኢትዮጵያን የሥኬት መንገድ በመከተል፣ አየር መንገዷን ከኪሳራ አውጥታ የቀጣናው ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ አልማለች። ይህ ትብብር በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከሩ ባለፈ፣ የአፍሪካ አገራት በራሳቸው አቅም እርስ በእርስ ለመደጋገፍ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያሳይ መሆኑ በዘገባው ተመላክቷል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories