በዓለማችን ቀዳሚ የፈሳሽ ተፈጥሮ ጋዝ አምራች የሆነችው ኳታር ምርቷን ማቋረጧን ተከትሎ፣ ህንድ ለኢንዱስትሪዎቿ የምታቀርበውን የጋዝ መጠን መቀነሷ ተሰማ።
ይህ ውሳኔ የተላለፈው በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ በመጣው ግጭት ምክንያት የኃይል አቅርቦት እጥረት ሊያጋጥም ይችላል በሚል ስጋት መሆኑን የዘርፉ ምንጮች ገልጸዋል።
እንደ ሮይተርስ ዘገባ ከሆነ፣ ኳታር የምርት ሂደቷን ያቆመችው ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ ሀገራት ላይ የምታደርገውን ጥቃት ተከትሎ ሲሆን፣ ይህም በሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በኩል የሚደረገውን የነዳጅ እና የጋዝ ትራንስፖርት አስተጓጉሏል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ አራተኛዋ ትልቅ የጋዝ ገዢ የሆነችው ህንድ፣ ከኳታር እና ከአቡ ዳቢ በሚመጣው አቅርቦት ላይ በእጅጉ ትመካለች። በዚህም ምክንያት የህንድ ትላልቅ የጋዝ አቅራቢ ኩባንያዎች (እንደ GAIL እና IOC ያሉ) ለደንበኞቻቸው ከ10% እስከ 30% የሚደርስ የአቅርቦት ቅናሽ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።
ይህን የአቅርቦት ጉድለት ለመሙላት የህንድ ኩባንያዎች የጋዝ ዋጋ፣ የጭነት እና የመድን ዋስትና ወጪዎች በከፍተኛ ሁኔታ ቢጨምሩም ከሌሎች አማራጭ ገበያዎች ጋዝ ለመግዛት ጨረታ ለማውጣት በዝግጅት ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
የግጭቱ መባባስ በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይም የ6% ጭማሪ ያስከተለ ሲሆን፣ ይህም የዓለምን የኢኮኖሚ ሁኔታ ይበልጥ አሳሳቢ እያደረገው ይገኛል።@SECO


