አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢዜማ መሪ ሆነው ተመረጡ

ፓርቲው የቀድሞውን  መሪውን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ምክትላቸውን በክብር ሸኝቷል

 አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመተካት የፓርቲው መሪ ሆነው ተመርጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ፓርቲውን ላለፉት ሰባት ዓመታት ሲመሩ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሰናብቶ እዮብ መሳፍንትን  የፓርቲው መሪ አድርጎ መርጧል።

ጠቅላላ ጉባዔውን በአድዋ መታሰቢያ አዳራሽ ያደረገው ኢዜማ  ከብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በተጨማሪ የፓርቲው ምክትል መሪ የነበሩትን አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንም በተመሳሳይ አሰናብቷል። በምትካቸውም አቶ ንጋቱ ወልዴ ተመርጠዋል፡፡

ፓርቲው ከመሪዎች ምርጫ በተጨማሪ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውን ያስተዋወቀ ሲሆን በቀጣይ የሚመራበትን 50 ፖሊሲዎችንም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories