ኢትዮ ቴሌኮም ግዙፍ የኔትወርክ ማስፋፊያዎችን ለማከናወን እና ለማዘመን የሚያስችል ስምምነት ከዜድ.ቲ.ኢ ጋር ተፈራረመ

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከኩባንያው ከፍተኛ የማኔጅመንት አመራሮች ጋር በመሆን በባርሴሎና በተካሄደው የ2026 የሞባይል ዓለም አቀፍ ኮንግረስ ጎን ለጎን፣ ከዜድ.ቲ.ኢ (ZTE) ኮርፖሬሽን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በዜድ.ቲ.ኢ የሥራ ቀጠና ውስጥ ግዙፍ የኔትወርክ ማስፋፊያ እና የማዘመን ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ስምምነትን ተፈራርመዋል።

ኢኒሸቲቩ 115 የገጠር ጣቢያዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 647 የኔትወርክ ጣቢያዎችን የሚያካትት ሲሆን፣ የኔትወርክ ተደራሽነት ለማሳደግ እና የኢትጵያን የዲጂታል አካታችነት ይበልጥ ለማስፋፋት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ተጠቁሟል።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ፣ የ4ጂ የሕዝብ ሽፋንን ወደ 95.5 በመቶ በማሳደግ የኔትወርክ አቅምን፣ ተደራሽነት እና የአገልግሎት ጥራትን በከፍተኛ ደረጃ ለመጨመር በተለይም ዘመናዊ የሞባይል ብሮድባንድ ኢንተርኔትን ወደ ገጠርና አገልግሎቱ ወዳልተዳረሰባቸው አካባቢዎች በማዳረስ  የዲጂታል አካታችነት ለማፋጠን ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሏል።

ስምምነቱ በዋናነት የኢትዮጵያን ሰፊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን አጀንዳን ለመደገፍ እና የዲጂታል ስነ-ምህዳሩን  በዘመናዊ፣ አስተማማኝ እና ለወደፊት ዝግጁ በሆኑ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማቶች በማስፋፋት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ዜጎች፣ ተቋማት እና ቢዝነሶች አቅምን ለማሳደግ  ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories