ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በስድስት ወራት ውስጥ የ66 ቢሊዮን ብር ሽያጭ ማከናወኑን አስታወቀ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ውስጥ 65.99 ቢሊየን ብር አጠቃላይ ሽያጭ በማከናወን ከዕቅድ በላይ ውጤት ማስመዝገቡን ገለጸ።

ተቋሙ በሸራተን አዲስ ሆቴል ባካሄደው የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ እንደተመለከተው፣ ይህ ውጤት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ71 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

በሪፖርቱ መሠረት ግሩፑ ካቀደው ትርፍ አንጻር 176 በመቶውን ማሳካት የቻለ ሲሆን፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ95 በመቶ ጭማሪ አለው።

በተጨማሪም ተቋሙ በስድስት ወራት ውስጥ ለውጭ ገበያ ካቀረባቸው ምርቶችና አገልግሎቶች ከ155 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ለሀገር ማስገኘቱ ተገልጿል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለማህበራዊና መንግስታዊ ግዴታዎች ያለውን ቁርጠኝነት ባሳየበት በዚህ ሪፖርት፣ ለግብርና ሌሎች መንግስታዊ ክፍያዎች ከ18.4 ቢሊዮን ብር በላይ እንዲሁም ለሠራተኞች ደመወዝ ከ4.5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማድረጉን አስታውቋል።

የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አሕመድ የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም በማርኬቲንግ፣ በምርት ጥራትና በወጪ ቅነሳ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚሠራ አሳስበዋል።

በአሁኑ ወቅት ከ45 በላይ ድርጅቶችን በስሩ አቅፎ የያዘው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ ከ80 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የቻለ ግዙፍ ተቋም መሆኑ ይታወቃል።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 220 ቦታዎች የሊዝ ጨረታ አወጣ

​የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በዘጠኝ ክፍለ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

ኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚዎችን ሾመ

አዲስ መዋቅር አስተዋውቋል የኢትዮ ቴሌኮም ሦስት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ...

Popular Categories