የአማራ ባንክ ከባለፈው ሙሉ አመት ካስመዘገበው ትርፍ በስምንት ወር ውስጥ 178 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ እንዳገኘ አስታወቀ

በኢቢቪ ዘጋቢ

ባንኩ በፋይናንስ ዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማስጠበቅ  እየሰራ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

ባንኩ በ2017 በጀት አመት ጥቅል ትርፍ 655 ሚሊየን ብር ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን   በ2018 በጀት ዓመት በስምንት ወራት ውስጥ 1.82 ቢሊዮን ብር ከግብር በፊት ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል፡፡

ይህም በ2017 ዓ.ም.የበጀት ዓመት ከተገኘው 655 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ትርፍ 178 በመቶ በላይ ብልጫ እድገት አሳይቷል።

የባንኩ አጠቃላይ ሀብተት 53 ቢሊዮን ብር ሲደርስ ይህም ከአምና ጋር ሲነፃፀር 10 ቢሊዮን ብር ገደማ ጭማሪ ማሳየቱን ባንኩ አስታውቋል፡፡

አማራ ባንክ የብድር ፖርትፎሊዮና የክሬዲት ተጋላጭነቱን አስመልክቶ ሙሉ በሙሉ በብሔራዊ ባንክ በተላለፉ የጥንቃቄ መመሪያዎች ገደብ ውስጥ ሆኖ በመፈፀም ላይ እንደሆነ ገልጿል፡፡

ባንኩ ለአንድ ተበዳሪ የሚሰጠው ጠቅላላ የብድር መጠን ብሄራዊ ባንክ ከፈቀደው የቁጥጥር ገደብ የ25 በመቶ በታች ሲሆን፣ ይህም የብሄራዊ ባንክን የአደጋ ስጋት መመሪያዎችን በጥብቅ በመከተል የተፈጸመ መሆኑን ጠቁሞ ወደ ባንኩ መጥተው አሁን ላይ ብድር ከወሰዱ የግለሰብ ደንበኞች ከ25 በመቶ በላይ  ብድር አለመስጠቱን አብራርቷል።

እ.ኤ.አ የ2025/26 በጀት ዓመት የስምንት ወራት አፈጻጸም ሪፖርት መሰረት ባንኩ የሀብት ጥራቱን ለማጠናከርና ለማሳደግ እየሰራ ሲሆን፣ የተበላሸ ብድር ምጣኔ (NPL) መጠንን ወደ 4.9 በመቶ ዝቅ ማድረግ ችያለሁ ብሏል ይህም በፋይናንስ ኢንዱስትሪውና በብሄራዊ ባንክ ተቀባይነት ያለዉ መጠን ዉስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነዉ፡፡

ባንኩ የብድር ክትትል፣ የአመላለስና የማገገም ስርዓቶች በመዘርጋቱ የፖርትፎሊዮ አፈፃፀሙ በከፍተኛ መጠን እንዲጠናከርና እንዲሻሻል ማድረጉን እና በዚህም ባለፉት ስምንት ወራት ብቻ ከ9.9 ቢሊዮን ብር በላይ ከብድር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቋል።

በባንኩ ውስጥ የአደጋ ስጋት አስተዳደርና የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቶች ቀጣይነት ባለው መልኩ እየተጠናከሩ ነው ያለው ባንኩ ይህም ዘላቂነት ያለው የብድር አቅርቦት እንዲኖር በማገዝ ላይ ነው ብሏል።

ባንኩ በአሁኑ ሰዓት የተለየ የጥሬ ገንዘብ እጥረት የሌለበት ሲሆን፣ ይህን ችግር ከፈታ ከአንድ ዓመት በላይ ማስቆጠሩንና በሞባይል ባንኪንግ አማካኝነት እስከ 1 ሚሊዮን ብር ድረስ ማስተላለፍ እንዲችሉ ማድረግ ተጭሏል ፡፡

በፋይናንስ አካታችነት ጉልህ ለውጥ በማስመዝገብ ላይ እንደሚገኝ ያስታወቀው አማራ ባንክ ከ 5.1 ቢሊዮን ብር በላይ በዲጂታል አነስተኛ ብድር መስጠቱን ከዚህ ውስጥ 90 በመቶው ለሴት ተበዳሪዎች እንደተሰጠ አስታውቆ በአጠቃላይ በዲጂታል አነስተኛ ብድር ከ240 ሺህ በላይ ደንበኞች ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን በመግለጫው አብራርቷል፡፡@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories