የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ከኩባንያው ከፍተኛ የሥራ አመራር ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን በጣሊያን ሮም ከሲዲፒ (Cassa Depositi e Prestiti – CDP) ከፍተኛ አመራሮች ጋር በስትራቴጂያዊ የትብብር መስኮችና ለታላላቅ የኢንቨስትመንት ፕሮግራሞች ሊገኝ በሚችል የፋይናንስ አጋርነት ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸውን ነው ካምፓኒው ያስታወቀው።
የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠንና የዲጂታል መሠረተ ልማት ሥነ-ምህዳር ለማስፋፋት ያለመውን የኩባንያችንን የ”ቀጣዩ አድማስ፡ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028″ ስትራቴጂን ለመተግበር የሚረዱ የፋይናንስ አማራጮችን ለማፈላለግ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።

መጠነ-ሰፊ የኔትወርክ ማስፋፊያና የማዘመን ሥራዎችን፣ የዲጂታልና የክላውድ መሠረተ ልማትን ማጠናከርን እንዲሁም እንደ ቴሌብር ያሉ የፈጠራ ውጤት የሆኑ ዲጂታል ፕላትፎርሞችንና የፋይናንስ አገልግሎቶችን የማሳደግ ውጥኖን ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አብራርተዋል።
የሲዲፒ አመራሮች በበኩላቸው ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ዓመታት ከመደበኛ ኦፕሬተርነት ወደ ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ኩባንያ ያደረገውን አስደናቂ ሽግግርና ፈጣን ዕድገት በማድነቅ፤ ኩባንያው በዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ውስጥ አርአያ የሚሆን ተሞክሮ መሆኑን ገልጸዋል።
የኔትወርክ ማስፋፊያ፣ የላቁ የዳታ ሴንተር ግንባታ፣ የታዳሽ ኃይል አማራጮች እንዲሁም በቴሌብር በኩል የሚከናወኑ የዲጂታል ግብርና ድጋፎችንና የአርሶ አደሮች የብድር አቅርቦት ሞዴሎችን ያካተተ የትብብር መስኮችም መቅረባቸውን ቅዳሜ ገበያ ከኢትዮ ቴኮም ያገኘቸው መረጃ ያሳያል፡፡@SECO


