ዳንጎቴ ግሩፕ ከቻይናው ጂ.ሲ.ኤል ጋር የ4.2 ቢሊዮን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ ስምምነት ተፈራረመ

አፍሪካዊው ቢሊየነር አሊኮ ዳንጎቴ በኢትዮጵያ ለሚገነባው ግዙፍ የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የሚውል የ4.2 ቢሊዮን ዶላር የተፈጥሮ ጋዝ አቅርቦት ስምምነት ከቻይናው ጂ.ሲ.ኤል ግሩፕ ጋር ተፈራርመዋል።

ለ25 ዓመታት የሚዘልቀው ይህ ስምምነት፣ በኢትዮጵያ በ2.5 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ለሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ የኃይልና የግብአት አቅርቦትን የሚያረጋግጥ ነው።

በዳንጎቴ ግሩፕ (60 በመቶ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (40 በመቶ) በጋራ የሚለማው ይህ ፋብሪካ፣ እ.አ.አ በ2029 ግንባታው ተጠናቆ ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ፋብሪካው ስራ ሲጀምር በዓመት 3 ሚሊዮን ቶን ዩሪያ የማምረት አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ይህም የምስራቅ አፍሪካ ግዙፉ ዘመናዊ የማዳበሪያ ማምረቻ ማዕከል ያደርገዋል።

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያን የአገር ውስጥ የማዳበሪያ ፍላጎት ከማሟላቱም ባለፈ፣ ምርቱን ለጎረቤት አገራት ገበያ ለማቅረብ ታቅዷል።

ዳንጎቴ በላጎስ በተከናወነው የፊርማ ስነ-ስርዓት ላይ እንደገለጹት፣ አፍሪካ ጥሬ ዕቃን ወደ ውጭ የመላክና ያለቀላቸውን ምርቶች የማስገባት ልምዷን መቀየር ይኖርባታል።

ይህ የስትራቴጂክ አጋርነት ከተፈጥሮ ጋዝ ቁፋሮ እስከ ማዳበሪያ ምርት ድረስ ያለውን ሰንሰለት በማስተሳሰር የአህጉሪቱን የግብርና እሴት እንደሚጨምር ገልጸዋል።

ይህ ግዙፍ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ለሚታየው የኢንዱስትሪ ልማት ከፍተኛ መነቃቃትን ከመፍጠሩም በላይ፣ ለሺዎች የሚቆጠር የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርና ኢትዮጵያ በማዳበሪያ ራሷን እንድትችል ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ የዘርፉ ባለሙያዎች እየገለጹ ይገኛሉ።@SECO

Related

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና ከፍተኛ የመንግስት የስራ  ሀላፊዎች ከኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ሀላፊነታቸው ተነሱ

ድርጅቱን በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩት የነበሩት አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ምክትል  ሰብሳቢ...

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የተሰጠው የእገዳ መመሪያ ውዝግብ አስነሳ​​

በኢትዮጵያ የሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ...

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች የሦስት እርከን የደመወዝ ጭማሪ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ጸደቀ

የሀገሪቱ ግዙፉ መንግሥታዊ የፋይናንስ ተቋም የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ...

አዳማ  የፈጣን ስማርት የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ  ተጠቃሚ  ሆነች

በአለምሰገድ እስጢፋኖስ ኢትዮ ቴሌኮም በዛሬው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ከአዲስ አበባ...

የኢትዮጵያ የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ተመረቀ

“ከማገዳችን በፊት ከአምስቴ በላይ ማስጠንቀቂያ ሰጥተናል!” የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ያስመረቀው...

Popular Categories