በኢቢቪ ዘጋቢ
ዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት (ሸሪክ) እና ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ነው የተፈራረሙት፡፡
ባንኩ በትራንስፖርትና የተለያዩ የንግድ ዘርፎች ተሰማርቶ ለሚገኘው ኤሌጋንስ አስመጪና ላኪ ድርጅት ለሜትር ታክሲ ትራንስፓርት አገልግሎት ለሚያውላቸው የመጀመሪያ ዙር እስከ 50 የሚደርሱ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ግዢ ከወለድ ነጻ በሆነ መንገድ ፋይናንስ እንደሚያመቻች ታውቋል፡፡
የዳሸን ባንክ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ተጠባባቂ ቺፍ ኦፊሰር አቶ አምዱ ሰማን እንደገለጹት ባንኩ በኢትዮጵያ የያንጎ ትራንስፖርት ቢዝነስ ለመስራት ልዩ ፈቃድ ካለው ኤሌጋንስ አስመጭና ላኪ ጋር የፈጸመው የመግባቢያ ስምምነት በሜትር ታክሲ ትራንስፓርት ዘርፍ የስራ ዕድሎችን ከፍ ለማድረግ ያግዛል፡፡

በተጨማሪም ፋይናንስ የሚደረጉት የኤሌክትሪክ ተሸርካሪዎች የአካባቢ ጥበቃን ማዕከል ያደረጉ በመሆናቸው ባንኩ ለአካባቢና ማህበረሰብ ደህንነት የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡
ስምንተኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው ሸሪክ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የተሻገረ ሲሆን አጠቃላይ ሃብቱ ደግሞ ከ26 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡@SECO


