በአለምሰገድ እስጢፋኖስ
ባንኩ በዛሬው ዕለት ስራ ያስጀመረው እስከ 6 ሚሊየን ብር የሚያሸልም የሱፐር አፕ ማስተዋወቅ ውድድርን ጨምሮ የዲጂታል ኢንቦርዲንግ አገልግሎት ፣ የዳሽን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም እንዲሁም ከማስተር ካርድ ጋር መተባበር የተለያዩ ዓለም አቀፍ ከፍያዎችን መክፈል የሚያስችል የዳሽን ቨርቹዋል ካርድ አገልግሎትን ነው ።
ዳሸን ባንክ የሱፐር አፕ ተጠቃሚዎችን ለማበረታት እንዲሁም የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማስፋት በማሰብ እጓጊ የቲክቶክ ይዘት ፈጠራ ውድድር (የሱፐር አፕ ክሬቲቭ አዋርድ) እንዳዘጋጀና በዚህ ውድድር ለሚያሽንፉ የይዘት ፈጣሪዎች በድምሩ ስድስት ሚሊዮን ብር የገንዘብ ሽልማት ማዘጋጀቱን ነው ያስታወቀው።

በዳሽን ስፐር እፕ ቲክቶክ ቻሌንጅ እሽናፊ ለመሆን ይዘት ፈጣሪዎች ስለ ዳሽን ባንክ ሱፐር አፕ አገልግሎቶች የሚገልፅ የቲክቶክ ቪዲዮ በመስራት ማጋራት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ የሰሩት ቪዲዮ በቲክቶክ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዕይታ ሲያገኝ) በዳሽን ሱፐር እፕ ውስጥ በሚገኘው የዳሽ ክሬቲቭ አዋርድ መተግበሪያ ድምፅ እንደሚሰጥበት ተገልጿል።
ከፍተኛ ደምፅ በማግኘት አንደኛ ለሚወጣ ይዘት ፈጣሪ 3 ሚሊዮን ብር፣ ሁለተኛ ለሚወጣ 2 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣ ዳሽን ባንክ 1 ሚሊዮን ብር እንደሚሸለም ተነግሯል።
በሌላ በኩል ባንኩ ይፋ ያደረገው የዳሽን ስታር ሪፈራል ፕሮግራም ሲሆን ፕሮግራሙ የዳሽን ሱፐር አፕ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች እንዲጠቀመብት በማድረግ የማበረታች ከፍያ እንዲያገኙ ለማስቻል የቀረበ አገልግሎት እንደሆነ ተጠቁሟል።
ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ አዲስ ታሪክ የፈጠረውን የዲጂታል ኦን ቦርዲንግ አገልግሎት ያስጀመረ ሲሆን አገልግሎቱም የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ በመጠቀም የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል።

ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር የተለያዩ ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መክፈል የሚያስችለው የዳሽን ቨርቹዋል ካርድ አገልግሎት ይፋ የተደረገ ሲሆን አገልግሎቲ በዳሸን ሱፐር አፕ ላይ የቀረበ የቨርቹዋል ካርድ ሲሆን፤ እንደ አሊባባ፣ አማዞን፤ ኔትፍሊክስን ጨምሮ ሌሎች ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችላል ተብሏል።
የዳሽን ባንክ ቨርቹዋል ካርድ ከዚህም በተጨማሪ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚላክ ሃዋላ መቀበል እንደሚያስችል ተገልጿል።@SECO


