በአፍሪካ ግዙፍ ተንቀሳቃሽነቱን እያሳየ የሚገኘው ራዲሰን ሆቴል ግሩፕ እ.ኤ.አ እስከ ኤፕሪል 2026 ድረስ ባለው መረጃ በአህጉሪቱ ከ30 በላይ በሚሆኑ ሀገራት የያዛቸውን የሆቴሎች ቁጥር ከ100 በላይ ማድረሱን አስታወቀ።
ኩባንያው ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ከ15 በላይ አዳዲስ ሆቴሎችንና 2,500 የመኝታ ክፍሎችን ወደ አገልግሎት በማስገባት አስደናቂ ዕድገት ማስመዝገቡ ተገልጿል።
ሆቴል ግሩፑ አሁን ላይ ትኩረቱን ወደ አዳዲስ ገበያዎች እያሰፋ ሲሆን፣ በተለይም በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና በዚምባብዌ አዳዲስ ስራዎችን ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል።
በዚሁ እቅዱ መሠረት በዚምባብዌ ቪክቶሪያ ፏፏቴ አቅራቢያ 150 የመኝታ ክፍሎች ያሉት “ፓርክ ኢን ባይ ራዲሰን” የተሰኘውን ሪዞርት እ.ኤ.አ በ2029 ለመክፈት አቅዷል።
ከዚህም በተጨማሪ ኩባንያው ወደ ዛንዚባር ለመግባት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ሲሆን በናሚቢያ፣ ቦትስዋና እና ዛምቢያ ያሉ የገበያ ዕድሎችንም በጥልቀት እየመረመረ ይገኛል።
በአሁኑ ወቅት ግብፅ በ143 ሆቴሎችና በ33,926 የመኝታ ክፍሎች የኩባንያውን የኢንቨስትመንት መስመር በግንባር ቀደምትነት እየመራች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ እና ታንዛኒያ በምስራቅ አፍሪካ በቀጣይ የኩባንያው ቁልፍ የዕድገት መዳረሻዎች ሆነው እንደሚቀጥሉ ተመልክቷል።@SECO


