አቶ አበበ አምሮ ሰላሴ በ IMF ስማቸው በጉልህ ከሚጠሩ የዘርፋ ባለሙያዎች መካከል ተጠቃሽ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
በለንደን ስመ ጥሩው የምጣኔ ሀብት ትምህርት ቤት London School of Economics (LSE) ትምህርታቸውን እንደተከታተሉ በሳቸው ዙሪያ የተጻፋ ድርሳናት ያሳያሉ።
እኤአ በ1994 IMF ጋር ከመቀላቀላቸው በፊት በኢትዮጵያ መንግስት መስሪያ ቤት ስራ የጀመሩ ሲሆን በሇላም በለንደን The Economist Intelligence Unit የኢኮኖሚ ትንታኔ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።
ይህም በኢኮኖሚክስ ስርዓት ትንታኔ እና በመመሪያ ፖሊሲ ስራዎች ላይ የተለያዩ የተግባር እውቀት እንዲቀስሙ አስችሏቸዋል።
አቶ አበበ አምሮ ሰላሴ እ.ኤ.አ ከ2016 ጀምሮ የኢንተርናሽናል ሞኒታሪ ፈንድ (IMF) የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር በመሆን የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የዕዳ አስተዳደር እና የአካባቢ ኢኮኖሚያዊ ልማት ስራዎች ላይ የተለያዩ ተግባራዊ ዕድገቶችን የመሪነት ሚና ያገኙ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
አቶ አበበ በአፍሪካ ከሚገኙ 45 ሀገራት ጋር የIMF የፖሊሲ ምክር፣ የብድር ፕሮግራሞች እና የቴክኒክ ድጋፍ ተግባራዊ ቅድሚያዎችን እየተቆጣጠሩ መምራት ችለዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ከአካባቢው ተቋማት ጋር የስትራቴጂክ አብሮነት እና ከፍተኛ የፖሊሲ ውይይት ለመገንባት ኀላፊነት ወስደው ሙያዊ ግዴታቸውን ተወጥተዋል።
አቶ አበበ አምሮ ሰላሴ ከአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር ከመሆናቸው በፊት በIMF ውስጥ ለ22 ዓመታት የቆየ ሙያዊ ልምድ ያካበቱ ጉምቱ ባለሙያ ናቸው።
በIMF በተለያዩ የስራ ዘርፎች ያገለገሉት አቶ አበበ የአፍሪካ ክፍል ዳይሬክተር (Deputy Director)፣ የፖርቱጋል እና የደቡብ አፍሪካ የልዑካን ቡድን መሪ (Mission Chief)፣ የክልል ጥናት ክፍል ኃላፊ (Division Chief, Regional Studies Division)፣ በኡጋንዳ የIMF የቋሚ ተወካይ (Senior Resident Representati) ሆነው አገልግለዋል።
አቶ አበበ በቱርክ፣ ታይላንድ፣ ሮማኒያ እና ኤስቶኒያ ላይ የነበሩ የIMF የብድር ፕሮግራሞች ላይ በመስራት አስተገብረዋል።
እንዲሁም በፖሊሲ እይታ፣ በኦፕሬሽን ግምገማ እና በኢኮኖሚያዊ ምርምር ስራዎች ላይ የተለያዩ ሚናዎችን መወጣት የቻሉ ባለሙያ ናቸው።
በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በተለያዩ የስራ ሀላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አበበ አእምሮ ስላሴ በሚያዚያ ወር ከድርጅቱ በጡረታ ይለያያሉ@SECO


