በኢቢቪ ዘጋቢ
ማንሰን ኢንቨስትመንትስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ለኢትዮጵያ ገበያ ተስማሚ የሆኑ ጥራት ያላቸው የሴራሚክ እና የፖርስሊን ምርቶችን በሀገር ውስጥ ለማስመረት እና ለማከፋፈል የሚያስችለውን ስትራቴጂያዊ ስምምነት ከቻይናው ባይጂያ የሴራሚክ አምራች ድርጅት ጋር ተፈራርሟል።
በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የንግድ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።
ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ቱለፋ አካባቢ ከ50 ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ኢንቨስትመንት የተገነባው የባይጂያ ፋብሪካ፣ በዓመት 14 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ምርቶችን የማምረት አቅም ያለው ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ ግዙፉ የሴራሚክ አምራች ያደርገዋል።
ፋብሪካው የሀገሪቱን ዓመታዊ የሴራሚክ ፍላጎት 70 በመቶ በመሸፈን ለውጭ ምንዛሬ መቆጠብ እና ለ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
የማንሰን ኢንቨስትመንትስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳዊት እርገቱ እና የባይጂያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ጃንግ ሁዋ አጋርነቱ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል።@SECO


